ስለዚህም ኢዮአስ ዮዳሄንና ሌሎቹንም ካህናት ወደ እርሱ ጠርቶ “ቤተ መቅደሱን ያላደሳችሁበት ምክንያት ምንድነው? ከዛሬ ጀምሮ የምትቀበሉትን ገንዘብ መያዝ የለባችሁም፤ ለቤተ መቅደሱ እድሳት ይውል ዘንድ ገንዘቡን አስረክቡ” አላቸው።
2 ዜና መዋዕል 23:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ በረታ፥ የመቶ አለቆቹንም፥ የይሮሐምን ልጅ ዓዛርያስን፥ የይሆሐናንንም ልጅ ይስማኤልን፥ የዖቤድንም ልጅ ዓዛሪያስን፥ የዓዳያንም ልጅ መዕሤያን፥ የዝክሪንም ልጅ ኤሊሳፋጥን ወስዶ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ በረታ፤ የመቶ አለቆች ከሆኑት ከይሮሐም ልጅ ከዓዛርያስ፣ ከይሆሐናን ልጅ ከይስማኤል፣ ከዖቤድ ልጅ ከዓዛርያስ፣ ከዓዳያ ልጅ ከማዕሤያ፣ ከዝክሪ ልጅ ከኤሊሳፋጥ ጋራ ቃል ኪዳን አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑ ዮዳሄ በሰባተኛው ዓመት የመቶ አለቆች ከነበሩት ከይሮሖም ልጅ ዐዛርያስ፥ ከይሆሐናን ልጅ እስማኤል፥ ከዖቤድ ልጅ ዐዛርያስ፥ ከዐዳያ ልጅ ማዕሴያና ከዚክሪ ልጅ ኤሊሻፋጥ ጋር ስምምነት ለማድረግ ብቃት ያለው መሆኑ ተሰማው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰባተኛውም ዓመት ኢዮአዳ በረታ፤ የመቶ አለቆቹንም፥ የኢዮራምን ልጅ አዛርያስን፥ የኢዮአናንም ልጅ እስማኤልን፥ የዖቤድንም ልጅ አዛርያን፥ የኢዳኢንም ልጅ መዓስያን፥ የዘካርያስንም ልጅ ኤሊሳፋጥን ወደ እግዚአብሔር ቤት ከእርሱ ጋር ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ በረታ፤ የመቶ አለቆቹንም፥ የይሮሐምን ልጅ ዓዛርያስን፥ የይሆሐናንንም ልጅ ይስማኤልን፥ የዖቤድንም ልጅ ዓዛሪያስን፥ የዓዳያንም ልጅ መዕሤያን፥ የዝክሪንም ልጅ ኤሊሳፋጥን ወስዶ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። |
ስለዚህም ኢዮአስ ዮዳሄንና ሌሎቹንም ካህናት ወደ እርሱ ጠርቶ “ቤተ መቅደሱን ያላደሳችሁበት ምክንያት ምንድነው? ከዛሬ ጀምሮ የምትቀበሉትን ገንዘብ መያዝ የለባችሁም፤ ለቤተ መቅደሱ እድሳት ይውል ዘንድ ገንዘቡን አስረክቡ” አላቸው።