ኢዮሣፍጥ ከእርሱ በፊት እንደነበረው እንደ አሳ በጌታ ፊት መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ ሠራ፤ ይሁን እንጂ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን አልደመሰሰም ነበር፤
2 ዜና መዋዕል 17:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልቡም በጌታ መንገድ ላይ ለመመላለስ ድፍረት ነበረው፤ የኮረብታውን መስገጃዎችና የማምለኪያ ዐፀዱንም ከይሁዳ አስወገደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልቡም በእግዚአብሔር መንገድ የጸና ነበር፤ እንደዚሁም ማምለኪያ ኰረብቶችንና የአሼራ ዐምዶችን ከይሁዳ አስወገደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ አገለገለ፤ ከዚህም በላይ በኰረብቶች ላይ የሚገኙትን የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችንና በይሁዳ የነበሩትን አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስሎች ሁሉ ደመሰሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልቡም በእግዚአብሔር መንገድ ከፍ ከፍ አለ፤ የኮረብታውን መስገጃዎችና የማምለኪያ አፀዱንም ከይሁዳ አስወገደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልቡም በእግዚአብሔር መንገድ ከፍ ከፍ አለ፤ የኮረብታውን መስገጃዎችና የማምለኪያ ዐፀዱንም ከይሁዳ አስወገደ። |
ኢዮሣፍጥ ከእርሱ በፊት እንደነበረው እንደ አሳ በጌታ ፊት መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ ሠራ፤ ይሁን እንጂ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን አልደመሰሰም ነበር፤
ይህም ሁሉ በተፈጸመ ጊዜ በዚያ የተገኙ እስራኤል ሁሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው ሁሉንም ፈጽመው እስከሚያጠፏቸው ድረስ ሐውልቶቹን ሰባበሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጡ፥ በይሁዳና በብንያምም ሁሉ ደግሞም በኤፍሬምና በምናሴ የነበሩትን የኮረብታው መስገጃዎችና መሠዊያዎች አፈረሱ። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወደ ርስታቸውና ወደ ከተሞቻቸው ተመለሱ።
ኤፍሬም ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ከጣዖታት ጋር እኔ ምን አደርጋለሁ? እኔ እመልስለታለሁ፥ ወደ እርሱም እመለከታለሁ፤ እኔ እንደ ለመለመ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህ በእኔ ዘንድ ይገኛል።