2 ዜና መዋዕል 17:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ወታደሮችን አኖረ፥ በይሁዳም አገር አባቱም አሳ በወሰዳቸው በኤፍሬም ከተሞች ዘበኞችን አስቀመጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ውስጥ ወታደር አኖረ፤ እንዲሁም በይሁዳ ምድርና አባቱ አሳ በያዛቸው በኤፍሬም መንደሮች ዘበኞች አስቀመጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞችና በየገጠሩ ሁሉ እንዲሁም አባቱ ንጉሥ አሳ ድል አድርጎ በያዛቸው በኤፍሬም ግዛት ባሉት ከተሞች ሁሉ ወታደሮቹን አሰፈረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ሠራዊቱን አኖረ፤ በይሁዳም ሀገር፥ አባቱም አሳ በወሰዳቸው በኤፍሬም ከተሞች መሳፍንቱን አስቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ወታደሮችን አኖረ፤ በይሁዳም አገር አባቱም አሳ በወሰዳቸው በኤፍሬም ከተሞች ዘበኞችን አስቀመጠ። |
አሳም እነዚህን ቃላትና የነቢዩን የዖዴድን ትንቢት በሰማ ጊዜ ልቡ ጸና፥ ከይሁዳና ከቢንያምም አገር ሁሉ በተራራማውም በኤፍሬም አገር ከያዛቸው ከተሞች ጸያፉን ነገር አስወገደ፤ በጌታም ቤት ፊት የነበረውን የጌታን መሠዊያ አደሰ።