አብራምም ወንድሙ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ የተወለዱትን ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ብላቴኖቹን አሰለፈ፥ ፍለጋቸውንም ተከትሎ እስከ ዳን ድረስ ሄደ።
2 ዜና መዋዕል 16:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወልደ አዴር ንጉሡን አሳን እሺ አለው፥ የሠራዊቱንም የጦር አዛዦች በእስራኤል ከተሞች ላይ ላከ፤ እነርሱም ዒዮንንና ዳንን፥ አቤልማይምንና ለንፍታሌም እንደ ግምጃ ቤት የሚያገለግሉትን ከተሞች ሁሉ ያዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤን ሃዳድም የንጉሥ አሳን ሐሳብ ተቀብሎ፣ የጦር አዛዦቹን በእስራኤል ከተሞች ላይ አዘመተ። እነርሱም ዒዮንን፣ ዳንን፣ አቤል ማይምንና የንፍታሌምን የዕቃ ግምጃ ቤት ከተሞችን ሁሉ ድል አድርገው ያዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ቤንሀዳድም አሳ ባቀረበለት ሐሳብ በመስማማት የጦር አዛዦቹንና ሠራዊቱን ልኮ በእስራኤል ከተሞች ላይ አደጋ እንዲጥሉ አደረገ፤ ሠራዊቱም ዒዮን፥ ዳን፥ አቤልቤትማዕካ ተብለው የሚጠሩትን ከተሞችና በንፍታሌም ግዛት ስንቅና ትጥቅ የሚቀመጥባቸውን ከተሞች ሁሉ በድል አድራጊነት ያዙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወልደ አዴርም ንጉሡን አሳን ሰማው፤ የሠራዊቱንም አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ ሰደደ፤ እነርሱም አእዮንንና ዳንን፥ አቤልማይምንና የንፍታሌምንም አውራጃ ከተሞች ሁሉ መቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤንሀዳድ ንጉሡን አሳን“እሺ” አለው፤ የሠራዊቱንም አለቆች በእስራኤል ከተሞች ላይ ሰደደ፤ እነርሱም ዒዮንንና ዳንን፥ አቤልማይምንና የንፍታሌምን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ መቱ። |
አብራምም ወንድሙ እንደ ተማረከ በሰማ ጊዜ በቤቱ የተወለዱትን ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ብላቴኖቹን አሰለፈ፥ ፍለጋቸውንም ተከትሎ እስከ ዳን ድረስ ሄደ።
ንጉሥ ቤንሀዳድም አሳ ባቀረበው ሐሳብ ተስማምቶ የጦር አዛዦቹንና ሠራዊቱን በመላክ በእስራኤል ከተሞች ላይ አደጋ እንዲጥሉ አደረገ፤ እነርሱም ዒዮን፥ ዳን፥ አቤልቤትማዕካና የገሊላ ባሕር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች በገሊላ ባሕር አጠገብ የሚገኘውን አገርና የንፍታሌምን ግዛት ሁሉ ያዙ።
እነዚህም የስንቅ ማከማቻዎች፥ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚጠበቁባቸው፥ ከተሞችን ከተመ፤ ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስና በግዛቱ ሁሉ የሚፈልገውን ገነባ።
የአካዝን ጥያቄ በመቀበል ቲግላት ፐሌሴር ዘምቶ ደማስቆን በቁጥጥሩ ሥር አደረገ፤ ንጉሥ ረጺንንም ገደለ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ቂር ተብላ ወደምትጠራው ስፍራ ወሰደው።
“በአባቴና በአባትህ መካከል እንደነበረው ቃል ኪዳን በእኔና በአንተ መካከል ይሁን፤ እነሆ፥ ብርና ወርቅ ልኬልሃለሁ፤ እርሱ ከእኔ ዘንድ እንዲርቅ ሄደህ ከእስራኤል ንጉሥ ከባኦስ ጋር ያለህን ቃል ኪዳን አፍርስ።”
ባዓላትንም፥ ለሰሎሞንም የነበሩትን ለግምጃ ቤት የሚያገለግሉ ከተሞች ሁሉ፥ የሠረገላውንም ከተሞች ሁሉ፥ የፈረሰኞችንም ከተሞች፥ በኢየሩሳሌምም በሊባኖስም በመንግሥቱም ምድር ሁሉ ሰሎሞን ለመሥራት የፈለገውን ሁሉ ሠራ።
ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፤ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከእምነት ፈቀቅ በማለት መንገዳቸውን ስተው ሄደዋል፥ በብዙም ሥቃይ ራሳቸውን ወግተዋል።
ከዚያም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እንዲሁም በገለዓድ ምድር የሚገኙ እስራኤላውያን ሁሉ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወጡ፤ በምጽጳም በጌታ ፊት ተሰበሰቡ።