2 ዜና መዋዕል 15:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድርም በሚኖሩት ሁሉ ላይ ታላቅ ሁከት ስለ ነበር በዚያም ዘመን ለሚወጣውና ለሚገባው ሰላም አልነበረውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ዘመን በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ዘንድ ታላቅ ሁከት ስለ ነበር፣ በሰላም ወጥቶ መግባት አስተማማኝ አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ በየስፍራው ሁሉ ሁከትና ሽብር ስለ ነበር፥ በሰላም ወጥቶ የሚገባ ማንም አልነበረም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ዘመን ለሚወጣውና ለሚገባው ሰላም አይሆንለትም፤ በሀገሮችም በሚኖሩት ሁሉ ላይ ታላቅ የእግዚአብሔር ቍጣ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ዘመን ለሚወጣውና ለሚገባው ሰላም አልነበረም፤ በምድርም በሚኖሩት ሁሉ ላይ ታላቅ ድንጋጤ ነበረ። |
ከነዚያ ወራት አስቀድሞ ለሰው ደሞዝ፥ ለእንስሳ ኪራይ አልነበረም፤ እኔም ሰውን ሁሉ በወንድሙ ላይ አስነሥቼ ስለ ነበር፥ በጠላቶቻቸው የተነሣ ወደዚያ ለሚገቡትና ለሚወጡት ሰላም አልነበራቸውም።
እስራኤላውያን ያሉበት ሁኔታ እጅግ አስጊ መሆኑንና ሠራዊታቸውም በከባድ ጭንቀት ውስጥ መግባቱን ባዩ ጊዜ፥ በየዋሻውና በየቁጥቋጦው፥ በየዐለቱ መካከልና በየገደሉ እንዲሁም በየጉድጓዱ ሁሉ ተሸሸጉ።