በፍጹምም ልባቸው ምለዋልና፥ በፍጹምም ሕሊናቸው ፈልገውታልና፥ እርሱም ተገኝቶላቸዋልና ይሁዳ ሁሉ በመሐላው ደስ አላቸው፤ ጌታም በዙሪያቸው እረፍት ሰጣቸው።
2 ዜና መዋዕል 15:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመከራቸውም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ ጌታ ተመልሰው በፈለጉት ጊዜ አገኙት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመከራቸው ጊዜ ግን፣ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መከራ በደረሰባቸው ጊዜ ግን ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ፊታቸውን መልሰው ፈለጉት፤ አገኙትም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመከራቸውም ጊዜ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ይፈልጉታል፤ እርሱም ይገኝላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመከራቸውም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው በፈለጉት ጊዜ አገኙት። |
በፍጹምም ልባቸው ምለዋልና፥ በፍጹምም ሕሊናቸው ፈልገውታልና፥ እርሱም ተገኝቶላቸዋልና ይሁዳ ሁሉ በመሐላው ደስ አላቸው፤ ጌታም በዙሪያቸው እረፍት ሰጣቸው።
አሳንም ሊያገኘው ወጣ፥ እንዲህም አለው፦ “አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ! ስሙኝ፤ እናንተ ከጌታ ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉትም ታገኙታላችሁ፤ ብትተውት ግን ይተዋችኋል።
ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ “የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል ወደ እኔ ተመለሱ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።”