2 ዜና መዋዕል 15:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልንም አምላክ ጌታን የማይፈልግ፥ ታናሽ ወይም ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን፥ እንዲገደል ማሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ ሁሉ ግን፣ ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ ወንድም ሆነ ሴት እንዲገደል አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የማያመልክ ማንም ወጣት ወይም ሽማግሌ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን በሞት የሚቀጣ መሆኑን በመሐላ ቃል አረጋገጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ፥ ታናሽ ወይም ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን፥ ይገደል ዘንድ ማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ፥ ታናሽ ወይም ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን፥ ይገደል ዘንድ ማሉ። |
ኤልያስም “የባዓልን ነቢያት ያዙ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዘ፤ሕዝቡም በሙሉ ያዛቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሾን ወንዝ እየመራ ወስዶ በዚያ ሁሉንም ገደላቸው።
እንዲህም ሆነ እኩለ ሌሊት ላይ ጌታ በግብጽ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ፥ በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኩር ጀምሮ በእስር ቤት እስካሉት እስከ እስረኞች በኩር ድረስ፥ የከብቶችንም በኩር ሁሉ መታ።
ከእግዚአብሔርም ዘንድ ረድኤት ተቀብዬ ለታናሹም ለታላቁም ስመሰክር እስከዚች ቀን ድረስ ቆሜአለሁ፤ ነቢያትና ሙሴ ይሆን ዘንድ ያለውን፥ ክርስቶስ መከራን እንዲቀበል በሙታንም ትንሣኤ ለሕዝብና ለአሕዛብ ብርሃንን በመጀመሪያ ሊሰብክ እንዳለው፥ ከተናገሩት በቀር አንድ ስንኳ የተናገርሁት የለም።”
የእነዚህን ሕዝቦች አማልክት ለማምለክ ልቡን ከጌታ ከእግዚአብሔር የሚመልስ ወንድም ሆነ ሴት ቤተሰብም ሆነ ነገድ ዛሬ ከመካከላችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ ከመካከልህ እንዲህ ያለውን መርዘኛና መራራ የሆነ ፍሬ የሚያበቅል አይገኝባችሁ።
ሙታንን፥ እንዲሁም ታላላቆችንና ታናናሾችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላም መጽሐፍ ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት በተጻፈው መሠረት፥ እንደ ሥራቸው መጠን ፍርድን ተቀበሉ።
የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም፥ ሀብታሞችም፥ ኃይለኞችም፥ አገልጋዮችም፥ ጌቶችም ሁሉ በዋሻዎችና በተራራዎች ዐለቶች ውስጥ ተሰወሩ፤