ከዚህም የተነሣ ሰሎሞን ኢዮርብዓምን ለመግደል ሞከረ፤ ነገር ግን ኢዮርብዓም ወደ ግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በመኰብለል አመለጠ፤ ሰሎሞንም እስከሞተበት ጊዜ ድረስ እዚያው ቆየ።
2 ዜና መዋዕል 12:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ላይ አልታመኑምና ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ ኢየሩሳሌምን ሊወጋት ወጣ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን ካለመታመናቸው የተነሣም፣ ሮብዓም በነገሠ በዐምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት በማጓደላቸውም ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ጣለበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብፅ ንጉሥ ሱስቀም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። እግዚአብሔርን በድለዋልና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርን በድለዋልና ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ ሺህ ሁለት መቶ ሠረገሎችና ስድሳ ሺህ ፈረሰኞች ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። |
ከዚህም የተነሣ ሰሎሞን ኢዮርብዓምን ለመግደል ሞከረ፤ ነገር ግን ኢዮርብዓም ወደ ግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ በመኰብለል አመለጠ፤ ሰሎሞንም እስከሞተበት ጊዜ ድረስ እዚያው ቆየ።
ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር ሶርያውያንን በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀበ የብዙ ሠራዊት ግሥጋሤ የሚመስል ድምፅ አሰምቶአቸው ስለ ነበር ነው፤ ይኸውም ሶርያውያን እንዳሰቡት የእስራኤል ንጉሥ የሒታውያንና የግብጽ ነገሥታትን ከነሠራዊቶቻቸው ቀጥሮ አደጋ ሊጥልባቸው የመጣ መስሎአቸው ነበር።
“አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይጥልሃል።
ለአሳም አላባሽ አግሬ ጋሻና ጦር የሚሸከሙ ሦስት መቶ ሺህ የይሁዳ ሠራዊት፥ ጋሻም የሚሸከሙ ቀስትም የሚገትሩ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ የብንያም ሰዎች ነበሩት፤ እነዚህም ሁሉ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ።
የአባቶቻቸውንም አምላክ ጌታን ትተው የማምለኪያ ዐፀዶችንና ጣዖታትን አመለኩ፤ በዚህ በደላቸውም ምክንያት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ቁጣ ወረደ።
መልእክተኞችን በባሕር ላይ፥ የደንገል መርከቦችንም በውኃ ላይ ለምትልክ ምድር ወዮላት! እናንተ ፈጣን መልእክተኞች ሆይ፥ ወደ ረጅምና ወደ ለስላሳ ሕዝብ፥ ከቅርብም ከሩቅም አስፈሪ ወደ ሆነ ሕዝብ፥ ኀያል ወደሆነና ወደሚገዛ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ ሂዱ።
ክፋትሽ ይቀጣሻል ክህደትሽ ይገሥጽሻል፤ ጌታን አምላክሽን መተውሽ ምን ያኽል ክፉና መራራ ነገር እንደሆነ እወቂም፥ ተመልከቺም፤ እኔን መፍራት በአንቺ ውስጥ የለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።