2 ዜና መዋዕል 11:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሦስት ዓመት በዳዊትና በሰሎሞን መንገድ ይሄዱ ነበርና ሦስት ዓመት የይሁዳን መንግሥት አበረቱ፥ የሰሎሞንንም ልጅ ሮብዓምን አጸኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚሁ ሁኔታ የዳዊትንና የሰሎሞንን መንገድ በመከተል፣ ለሦስት ዓመት የይሁዳን መንግሥት አበረቱ፤ የሰሎሞንን ልጅ ሮብዓምንም ረዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ሁኔታ የይሁዳን መንግሥት አጠናከረ፤ ሦስት ዓመት ሙሉም የሰሎሞንን ልጅ ሮብዓምን ረዱ፤ የንጉሥ ዳዊትንና የንጉሥ ሰሎሞንን መንገድ ተከትለው በሰላም ኖሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሦስት ዓመትም በዳዊትና በሰሎሞን መንገድ ይሄድ ነበርና ሦስት ዓመት የይሁዳን መንግሥት አበረቱ፤ የሰሎሞንንም ልጅ ሮብዓምን አጸኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሦስት ዓመት በዳዊትና በሰሎሞን መንገድ ይሄዱ ነበርና ሦስት ዓመት የይሁዳን መንግሥት አበረቱ፤ የሰሎሞንንም ልጅ ሮብዓምን አጸኑ። |