አቤሴሎምና የእስራኤል ሰዎች ሁሉም “ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የአርካዊው የሑሻይ ምክር ይሻላል” አሉ፤ ጌታ በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ለማምጣት፥ ጌታ መልካም የነበረው የአኪጦፌል ምክር ተቀባይነት እንዲያጣ አድርጎአል።
2 ዜና መዋዕል 10:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን ሽማግሌዎች የመከሩትን ነገር ትቶ ከእርሱ ጋር ካደጉትና በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ብላቴኖች ጋር ተማከረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሮብዓም ግን ሽማግሌዎች የሰጡትን ምክር ንቆ፣ ዐብሮ አደጎቹና አገልጋዮቹ ከሆኑት ወጣቶች ምክር ጠየቀ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሮብዓም ግን የሽማግሌዎቹን ምክር ቸል በማለት ቀድሞ አብሮ ዐደጎቹና አገልጋዮቹ የነበሩትን ጠርቶ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን ሽማግሌዎች የመከሩትን ነገር ትቶ ከእርሱ ጋር ካደጉትና በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ብላቴኖች ጋር ተማከረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን ሽማግሌዎች የመከሩትን ነገር ትቶ ከእርሱ ጋር ካደጉትና በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ብላቴኖች ጋር ተማከረ። |
አቤሴሎምና የእስራኤል ሰዎች ሁሉም “ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የአርካዊው የሑሻይ ምክር ይሻላል” አሉ፤ ጌታ በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ለማምጣት፥ ጌታ መልካም የነበረው የአኪጦፌል ምክር ተቀባይነት እንዲያጣ አድርጎአል።
ለዓመፀኞች ልጆች ወዮላቸው! ይላል ጌታ፤ ከእኔ ዘንድ ያልሆነን ምክር ይመክራሉ፥ ኃጢአትንም በኃጢአት ላይ ለመጨመር ከመንፈሴ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ።