2 ዜና መዋዕል 10:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እነርሱም እንዲህ ብለው ተናገሩት፦ “ለዚህ ሕዝብ ቸርነት ብታደርግላቸው፥ ደስም ብታሰኛቸው፥ በገርነትም ብትናገራቸው፥ ለዘለዓለም ባርያዎች ይሆኑልሃል።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 እነርሱም፣ “ለዚህ ሕዝብ ደግ ከሆንህለት፣ ደስ ካሠኘኸውና የሚስማማውን መልስ ከሰጠኸው ምን ጊዜም አገልጋይህ ይሆናል” ብለው መለሱለት። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ሽማግሌዎቹም “ለእነርሱ ደግነትን ብታሳያቸው፥ ለጥያቄአቸውም ተስማሚ የሆነ መልስ በመስጠት ደስ ብታሰኛቸው፥ እነርሱ ዘወትር በታማኝነት ያገለግሉሃል” ሲሉ መለሱለት። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 እነርሱም፥ “በዚች ዕለት ለዚህ ሕዝብ ቸርነት ብታደርግላቸው፥ ደስም ብታሰኛቸው፥ መልካም ነገርንም ብትናገራቸው፥ ሁልጊዜ አገልጋዮች ይሆኑልሃል” ብለው ተናገሩት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 እነርሱም “ለዚህ ሕዝብ ቸርነት ብታደርግላቸው፥ ደስም ብታሰኛቸው፥ በገርነትም ብትናገራቸው፥ ለዘላለም ባሪያዎች ይሆኑልሃል” ብለው ተናገሩት። Ver Capítulo |