2 ዜና መዋዕል 1:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሆርም ልጅ የኡሪ ልጅ ባስልኤል የሠራው የናስ መሠዊያ በዚያ በጌታ ማደሪያ ፊት ነበረ፤ ሰሎሞንም ጉባኤውም ይህን ይፈልጉት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ የሑር ልጅ፣ የኡሪ ልጅ ባስልኤል የሠራው መሠዊያ በገባዖን በእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳን ፊት ለፊት ይገኝ ነበር፤ ስለዚህ ሰሎሞንና ጉባኤው ይህንኑ ፈለጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሑር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባጽልኤል ከነሐስ የሠራው መሠዊያም በዚያው በገባዖን በድንኳኑ ፊት ለፊት ነበረ፤ በዚያም ንጉሥ ሰሎሞንና ሕዝቡ ሁሉ ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሆርም ልጅ የኡሪ ልጅ ባስልኤል የሠራው የናስ መሠዊያ በዚያ በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት ነበረ፤ ሰሎሞንና የእስራኤልም ጉባኤ የእግዚአብሔርን ታቦት ይፈልጓት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሆርም ልጅ የኡሪ ልጅ ባስልኤል የሠራው የናስ መሠዊያ በዚያ በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት ነበረ፤ ሰሎሞንም ጉባኤውም ይህን ይፈልጉት ነበር። |