1 ጢሞቴዎስ 3:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ማንም ኤጲስ ቆጶስነት ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል፤” የሚለው ቃል የታመነ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ማንም ኤጲስቆጶስነትን ቢፈልግ፣ መልካም ሥራን ይመኛል” የሚለው ቃል የታመነ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው “ኤጲስ ቆጶስ (የቤተ ክርስቲያን መሪ) ለመሆን ቢፈልግ ክቡር ሥራን ይመኛል” የሚለው ቃል እውነተኛ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል፤” የሚለው ቃል የታመነ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል የሚለው ቃል የታመነ ነው። |
በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
የኢየሱስ ክርስቶስ ባርያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ፥ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤
“ኀጢአተኞችን ለማዳን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ፤” የሚለው ቃል የታመነና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋነኛው እኔ ነኝ፤
ኤጲስ ቆጶስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ ነቀፋ የሌለበት ሊሆን ይገባዋል፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ ጠበኛ ያልሆነ፥ ለገንዘብ የማይስገበገብ፥
ቃሉ የታመነ ነው። እግዚአብሔርንም የሚያምኑት በመልካም ሥራ በጥንቃቄ እንዲተጉ፥ እነዚህን አስረግጠህ እንድትናገር እፈቅዳለሁ። ይህ መልካምና ለሰዎች የሚጠቅም ነው፤
ማንም ከእናንተ መካከል እንደ ነፍሰ ገዳይ፥ ወይም እንደ ሌባ፥ ወይም እንደ ክፉ አድራጊ፥ ወይም በሌሎች ጉዳይ ጣልቃ እንደሚገባ ሆኖ መከራ የሚቀበል አይኑር።
ኀላፊነት የተሰጣችሁን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ ይህም በግድ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ፍላጎት በፈቃደኝነት፥ ለጥቅም በመስገብገብ ሳይሆን በጽኑ ፍላጎት ይሁን፤