La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 9:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ በተራራማው በኤፍሬም አገርና በሻሊሻ አካባቢ ባለው ስፍራ ሁሉ ተዘዋወረ፤ ሆኖም አህዮቹን አላገኘም። ወደ ሻዕሊምም ግዛት ዘልቀው ገቡ፤ አህዮቹ ግን በዚያም አልነበሩም። ከዚያም በብንያም ምድር በኩል አለፉ፤ ሆኖም አላገኟቸውም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ በኰረብታማው በኤፍሬም አገርና በሻሊሻ አካባቢ ባለው ስፍራ ሁሉ ተዘዋወረ፤ ሆኖም አህዮቹን አላገኙም። ወደ ሻዕሊምም ግዛት ዘልቀው ገቡ፤ አህዮቹ ግን በዚያም አልነበሩም። እንዲሁም በብንያም ግዛት በኩል ዐለፈ፤ ሆኖም አላገኟቸውም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳኦልና አገልጋዩም ተነሥተው በተራራማው የኤፍሬም አገርና በሻሊሻ ምድር በኩል አልፈው አህዮቹን መፈለግ ጀመሩ፤ ነገር ግን አህዮቹን ማግኘት አልቻሉም፤ ከዚያም በሻዕሊም ምድር በኩል አልፈው ሳያገኙአቸው ቀሩ፤ እንደገናም በብንያም ግዛት በኩል አለፉ፤ ይሁን እንጂ አሁንም አህዮቹን ማግኘት አልቻሉም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ተራ​ራ​ማ​ውም ወደ ኤፍ​ሬም ሀገር ሄዱ፤ በሲ​ልካ ምድ​ርም አለፉ፤ አላ​ገ​ኙ​አ​ቸ​ው​ምም፤ በፋ​ስ​ቂም ምድር አለፉ፤ በዚ​ያም አል​ነ​በ​ሩም፤ በኢ​ያ​ሚ​ንም ምድር አለፉ፤ አላ​ገ​ኙ​አ​ቸ​ው​ምም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በተራራማው በኤፍሬም አገርና በሻሊሻ አለፉ፥ አላገኙአቸውምም፥ በሻዕሊም ምድርም አለፉ፥ በዚያም አልነበሩም፥ በብንያም ምድርም አለፉ፥ አላገኙአቸውምም።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 9:4
9 Referencias Cruzadas  

ያዕቆብም፥ ከፓዳን-ኣሪም በተመለሰ ጊዜ፥ በከነዓን ምድር ወዳለችው፥ ሴኬም ከተማ በሰላም መጣ፥ እናም በከተማይቱ ፊት ለፊት ሰፈረ።


ሌላም ጊዜ በዓልሻሊሻ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ አንድ ሰው በመከር ጊዜ በመጀመሪያ ከተወቃው ገብስ የተጋገሩ ኻያ የዳቦ ሙልሙሎችና አዲስ የተቆረጠ እሸት ለኤልሳዕ ይዞለት መጣ፤ ኤልሳዕም “ለነቢያት ጉባኤ አቅርብላቸውና ይብሉ” ብሎ አገልጋዩን አዘዘው፤


ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን፥ በዚያ ብዙ ውሃ ነበርና፥ ያጠምቅ ነበር፤ እየመጡም ይጠመቁ ነበር፤


ሸዕለቢንን፥ ኤሎንን፥ ይትላን፥


የአሮንም ልጅ አልዓዛር ሞተ፤ በተራራማውም በኤፍሬም አገር ለልጁ ለፊንሐስ በተሰጠችው በጊብዓ መሬት ቀበሩት።


ሚካ የተባለ በኰረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖር ሰው ነበር።


በዚያን ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ በዚሁ ጊዜም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖር አንድ ሌዋዊ ከይሁዳ ምድር ከቤተልሔም አንዲቱን ሴት ቁባት አድርጎ ወሰዳት።


በተራራማው በኤፍሬም አገር በአርማቴም መሴፋ የሚኖር ሕልቃና የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊዩ ልጅ፥ የቶሑ ልጅ፥ የናሲብ ልጅ ሲሆን ከኤፍሬም ነገድ ነበረ።


በዚያም ጊዜ የሳኦል አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦልን፥ “ከአገልጋዮቹ መካከል አንዱን ይዘህ ሂድና አህዮቹን ፈልግ” አለው።