La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት የምትመልሱ ከሆነ ከበደል መሥዋዕት ጋር ስደዱት እንጂ ባዶውን አትስደዱት፤ በዚያን ጊዜ ትፈወሳላችሁ፤ እጁም ከእናንተ ላይ ለምን እንዳልተነሣ ታውቃላችሁ” አሏቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም፣ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት የምትመልሱ ከሆነ ከበደል መሥዋዕት ጋራ ስደዱት እንጂ ባዶውን አትስደዱት፤ በዚያ ጊዜ ትፈወሳላችሁ፤ እጁም ከእናንተ ላይ ለምን እንዳልተነሣ ታውቃላችሁ” አሏቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “የእስራኤልን አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት መልሳችሁ ለመላክ ብትፈልጉ፥ ስለ በደላችሁ የሚከፈል ስጦታ አብራችሁ መላክ ይገባችኋል፤ የቃል ኪዳኑ ታቦት ያለ ምንም ስጦታ ተመልሶ መሄድ የለበትም፤ በዚህም ዐይነት እናንተ ከሕመማችሁ ትፈወሳላችሁ፤ እርሱ እናንተን በብርቱ የቀጣበትንም ምክንያት ልታውቁ ትችላላችሁ።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ር​ሱም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ብት​ሰ​ድ​ዱ​አት ስለ አሳ​ዘ​ና​ች​ሁ​አት የበ​ደል መባእ ስጡ እንጂ ባዶ​ዋን አት​ስ​ደ​ዱ​አት፤ የዚ​ያን ጊዜም ትፈ​ወ​ሳ​ላ​ችሁ፤ ስር​የ​ትም ይደ​ረ​ግ​ላ​ች​ኋል፤ አለ​ዚያ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ከእ​ና​ንተ አይ​ር​ቅም” አሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም፦ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ብትሰድዱ የበደል መሥዋዕት መልሱለት እንጂ ባዶውን አትስደዱት፥ የዚያን ጊዜም ትፈወሳላችሁ፥ እጁም ከእናንተ አለመራቁ ስለ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ አሉ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 6:3
15 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ አትፍረድብኝ፥ የምትከራከረኝ ለምን እንደሆነ ንገረኝ።


የቂጣውን በዓል ጠብቅ፤ በተመደበው በአቢብ ወር ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ እንዳዘዝሁህ ትበላለህ፤ በዚህ ወር ከግብጽ ምድር ወጥታችኋልና፥ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ።


የአህያውን በኩር በጠቦት ትዋጀዋለህ፥ ካልዋጀኸው ግን አንገቱን ትሰብረዋለህ። የልጆችህንም በኩር ሁሉ ትዋጃለህ። በፊቴ አንድ ሰው ባዶ እጁን አይታይ።


አስማተኞቹም ፈርዖንን፦ “ይህስ የእግዚአብሔር ጣት ነው” አሉት፤ የፈርዖን ልብ ግን ደነደነ፥ ጌታም እንደ ተናገረ አልሰማቸውም።


ስለ ሠራው ኃጢአት ለጌታ የበደል መሥዋዕት ያመጣል፤ እርሱም ከመንጋው የበግ ወይም የፍየል እንስት ለኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል፤ ካህኑም ስለ ኃጢአቱ ያስተሰርይለታል።


ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ ለበደል መሥዋዕት፥ ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ፥ ለጌታ ስለ በደሉ መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣል።


“በዓመት ሦስት ጊዜ ወንዶች ሁሉ በቂጣ በዓል፥ በመከርንና በዳስ በዓል፥ በአምላክህ በጌታ ፊት እርሱ በመረጠው ስፍራ ይታዩ፥ በጌታም ፊት ባዶ እጃቸውን አይታዩ።


የእግዚአብሔር እጅ በርትቶባቸው ስለ ነበር፥ ሞት ከተማዪቱን እጅግ አስደንግጧት ነበርና ሕዝቡ የፍልስጥኤማውያንን ገዢዎች በሙሉ ጠርተው፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ከዚህ አርቁልን፤ ወደ ገዛ ስፍራው ይመለስ፤ ያለበለዚያ እኛንም ሕዝባችንንም ይፈጃል” አሉ።


የአሽዶድ ሰዎች ይህን ባዩ ጊዜ፥ “እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጠንክሯልና የእስራኤል አምላክ ታቦት በእኛ ዘንድ መቆየት የለበትም” አሉ።


ነገር ግን ታቦቱን ወደዚያ ከወሰዱትም በኋላ የጌታ እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፤ ታላቅ መሸበርም አመጣባቸው፤ ሕፃን ሽማግሌ ሳይል ሕዝቡን በእባጭ መቅሠፍት መታ።


የጌታን ታቦት ወስዳችሁ በሠረገላው ላይ አኑሩ፤ ስለ በደልም መሥዋዕት ያቀረባችሁትን ልዩ ልዩ የወርቅ ዕቃ በሣጥን ውስጥ አድርጋችሁ በታቦቱ አጠገብ አኑሩት፤ መንገዱንም እንዲሄድ ልቀቁት።


ከዚያም ወዴት እንደሚሄድ ተመልከቱ፤ ወደ ገዛ አገሩ ወደ ቤትሼሜሽ አቅጣጫ የሚሄድ ከሆነ፥ ይህን ታላቅ መከራ ያመጣብን እርሱ ነው። ወደዚያ ካልሄደ ግን፥ መከራው በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የእርሱ እጅ እንዳልመታን እናውቃለን።”