La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 30:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም በምድረ በዳ አንድ ግብፃዊ አገኙ፤ ወደ ዳዊትም አመጡት። የሚጠጣውን ውሃና የሚበላውን ምግብ ሰጡት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም በምድረ በዳ አንድ ግብጻዊ አገኙ፤ ወደ ዳዊትም አመጡት፤ የሚጠጣውን ውሃና የሚበላውን ምግብ ሰጡት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንድ ግብጻዊ ወጣት ከበረሓ ሲመጣ አግኝተው ወደ ዳዊት አቀረቡት፤ እነርሱም የሚመገበው እህል ሰጥተውት በላ፤ ውሃም አጠጡት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በበ​ረ​ሃ​ውም ውስጥ አንድ ግብ​ፃዊ አግ​ኝ​ተው ወደ ዳዊት ይዘ​ውት መጡ፤ እን​ጀ​ራም ሰጡ​ትና በላ፤ ውኃም አጠ​ጡት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በበረሀውም ውስጥ አንድ ግብጻዊ አግኝተው ወደ ዳዊት ይዘውት መጡ፥ እንጀራም ሰጡትና በላ፥ ውኃም አጠጡት፥

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 30:11
9 Referencias Cruzadas  

ጠላትህ ቢራብ እንጀራ አብላው፥ ቢጠማም ውኃ አጠጣው፥


ተርቤ አብልታችሁኛልና፤ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል፤ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛል፤


“ኤዶማዊ ወንድምህ ነውና አትጸየፈው፥ ግብፃዊውንም በአገሩ ስደተኛ ነበርህና አትጸየፈው።


ከእነርሱም በሦስተኛው ትውልድ የሚወለዱ ልጆች ወደ ጌታ ጉባኤ ይግቡ።”


ሁለት መቶዎቹ እጅግ ዝለው ስለ ነበር ወንዙን መሻገር አልቻሉም። ነገር ግን ዳዊትና አራት መቶ ሰዎች መከታተላቸውን ቀጠሉ።


እንደዚሁም የበለስ ጥፍጥፍ ቁራሽና ሁለት ደረቅ የወይን ዘለላዎች ሰጡት። ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ምንም እህል ስላልበላ፥ ውሃም ስላልጠጣ ይህን ከበላ በኋላ ነፍሱ ተመለሰች።