1 ሳሙኤል 25:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋዮቹም ወደ ቀርሜሎስ ሄደው አቢጌልን፥ “ሚስት ትሆኚው ዘንድ እንድንወስድሽ ዳዊት ወደ አንቺ ልኮናል” አሏት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋዮቹም ወደ ቀርሜሎስ ሄደው አቢግያን፣ “ሚስት ትሆኚው ዘንድ እንድንወስድሽ ዳዊት ወደ አንቺ ልኮናል” አሏት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልጋዮቹም እርስዋ ወዳለችበት ወደ ቀርሜሎስ ሄደው “ሊያገባሽ ስለ ፈቀደ ወደ ዳዊት ልንወስድሽ መጥተናል” አሉአት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊትም ብላቴኖች ወደ ቀርሜሎስ ወደ አቤግያ መጡ፥ “ዳዊትም ሚስት ትሆኚው ዘንድ ወደ አንቺ ልኮናል” ብለው ነገሩአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊትም ባሪያዎች ወደ ቀርሜሎስ ወደ አቢግያ በመጡ ጊዜ፦ ዳዊት ያገባሽ ዘንድ ወደ አንቺ ልኮናል ብለው ነገሩአት። |
ዳዊትም ናባል መሞቱን በሰማ ጊዜ፥ “የናባልን ስድብ የተበቀለልኝና እኔን አገልጋዩን ክፉ ከማድረግ የጠበቀኝ ጌታ ይመስገን፤ ናባል የሠራውንም ክፉ ነገር በራሱ ላይ መለሰበት” አለ። ዳዊትም አቢጌል ሚስት ትሆነው ዘንድ በመጠየቅ መልእክት ላከባት።
እርሷም ተነሥታ በግምባሯ በመደፋት እጅ ከነሣች በኋላ፥ “እነሆ፤ እኔ አገልጋይህ አንተን ለማገልገል፥ የጌታዬንም አገልጋዮች እግር ለማጠብ ዝግጁ ነኝ” አለች።