1 ሳሙኤል 25:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰውየው ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቢጌል ነበረ። እርሷም አስተዋይና ውብ ነበረች፤ ባሏ ግን ባለጌና ምግባረ ብልሹ ሰው ነበረ፤ እርሱም ከካሌብ ወገን ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰውየው ስም ናባል፣ የሚስቱም ስም አቢግያ ነበረ። እርሷም አስተዋይና ውብ ነበረች፤ ባሏ ግን ባለጌና ምግባረ ብልሹ ሰው ነበረ፤ እርሱም ከካሌብ ወገን ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰውዬውም ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቤግያ ነበረ፤ ሴቲቱም ደግና ብልህ፥ መልክዋም እጅግ የተዋበ ነበረ፤ ሰውዬው ግን ጨካኝና ንፉግ ነበረ፤ ግብሩም ክፉ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰውዮውም ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቢግያ ነበረ፥ የሴቲቱም አእምሮ ታላቅ፥ መልክዋም የተዋበ ነበረ፥ ሰውዮው ግን ባለጌ ነበረ፥ ግብሩም ክፉ ነበረ፥ ከካሌብም ወገን ነበረ። |
ጌታም ኢያሱን እንዳዘዘው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ በይሁዳ ልጆች መካከል ቂርያት-አርባቅ የምትባለውን ከተማ ድርሻ አድርጎ ሰጠው፤ እርሷም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።
አሁንም በጌታችንና በመላው ቤተሰቡ ላይ መከራ እያንዣበበ ስለሆነ፥ ምን እንደምታደርጊ አስቢበት፤ እርሱ እንደሆነ እንዲህ ያለ ባለጌ ሰው ስለሆነ፥ ማንም ደፍሮ የሚነግረው የለም።”
ጌታዬ፥ ያን ባለጌ ሰው ናባልን ከቁምነገር አይቁጠረው፤ ስሙ ራሱ ሞኝ ማለት ስለሆነ፥ ሰውየውም ልክ እንደ ስሙ ነው፤ ሞኝነትም አብሮት የኖረ ነው። እኔ አገልጋይህ ግን ጌታዬ የላካቸውን ጐልማሶች አላየኋቸውም።