Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢያሱ 15:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ጌታም ኢያሱን እንዳዘዘው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ በይሁዳ ልጆች መካከል ቂርያት-አርባቅ የምትባለውን ከተማ ድርሻ አድርጎ ሰጠው፤ እርሷም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ኢያሱ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት፣ ከይሁዳ ድርሻ ላይ ከፍሎ ኬብሮን የተባለችውን ቂርያት አርባቅን ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ሰጠው፤ አርባቅም የዔናቅ አባት ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔር ኢያሱን ባዘዘው መሠረት ለይፉኔ ልጅ ለካሌብ ከይሁዳ ነገድ ኪርያት ዐርባን ወይም ኬብሮን እርስት አድርጎ ሰጠው። (አርባ የዐናቅ አባት ነበር)

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ለዮ​ፎኒ ልጅ ለካ​ሌብ በይ​ሁዳ ልጆች መካ​ከል ድር​ሻ​ውን ሰጠው፤ ኢያ​ሱም የዔ​ናቅ ዋና ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን የአ​ር​ቦ​ቅን ከተማ ሰጠው። እር​ስ​ዋም ኬብ​ሮን ናት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዳዘዘው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ በይሁዳ ልጆች መካከል ቂርያትአርባቅ የምትባለውን ከተማ ድርሻ አድርጎ ሰጠው፥ እርስዋም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 15:13
18 Referencias Cruzadas  

ካሌብም ሕዝቡን በሙሴ ፊት ዝም አሰኘና፦ “ማሸነፍ እንችላለንና እንውጣ፥ እንውረሰው” አለ።


በከነዓንም ምድር ባለችው ቂርያት-አርባዕ ተብላ በምትጠራው በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃምም ለሣራ ሊያዝንላትና ሊያለቅስላት ተነሣ።


ከይሁዳ ነገድ የዮፎኒ ልጅ ካሌብ፤


በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርያት-አርባቅ የምትባለውን ከተማ በዙሪያዋም ያለውን መሰማሪያ ሰጡአቸው፤ እርሷም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።


የይሁዳ ሰዎች በኬብሮን በሚኖሩ ከነዓናውያን ላይ ዘመቱ፤ ኬብሮን ቀደም ሲል ቂርያት-አርባዕ ተብላ ትጠራ ነበር፤ እነርሱም ሼሻይን፥ አሒማንንና ታልማይኖችን ድል አደረጉ።


የሰውየው ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቢጌል ነበረ። እርሷም አስተዋይና ውብ ነበረች፤ ባሏ ግን ባለጌና ምግባረ ብልሹ ሰው ነበረ፤ እርሱም ከካሌብ ወገን ነበር።


የከሪታውያንን ደቡብ፥ የይሁዳን ግዛትና የካሌብን ደቡብ ወረርን፤ ጺቅላግንም በእሳት አጋየናት።”


የከተማይቱን እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ሰጡ።


አብራምም ድንኳኑን ነቀለ መጥቶም በኬብሮን ባለው በመምሬ የባሉጥ ዛፎች ተቀመጠ፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ።


በዚያን ጊዜም ኢያሱ መጣ፥ ከተራራማውም አገር ከኬብሮንም ከዳቤርም ከአናብም ከእስራኤልም ተራራማ ሁሉ ከይሁዳም ተራራማ ሁሉ የዔናቅን ልጆች ገደለ፤ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው።


በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት-አርባቅን ለዩ።


ሙሴም እንደ ተናገረው ኬብሮን ለካሌብ ተሰጠች፤ እርሱም ሦስቱን የዐናቅ ልጆች ከውስጧ አሳደደ።


በኬብሮን ለነበሩ፥ ዳዊትና ሰዎቹም በተመላለሱበት ስፍራ ለነበሩ ሁሉ ላከላቸው።


ከዚህ በኋላ ዳዊት፥ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን?” ብሎ ጌታን ጠየቀ። ጌታም፥ “አዎን ውጣ” አለው። ዳዊትም፥ “ወደ የትኛዪቱ ልሂድ?” ሲል ጠየቀ። እርሱም፥ “ወደ ኬብሮን” ብሎ መለሰለት።


ጾርዓን፥ ኤሎንን፥ ኬብሮንን ሠራ፤ እነዚህም የተመሸጉ ከተሞች በይሁዳና በብንያም የሚገኙ ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios