1 ሳሙኤል 24:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ሰዎቹን በዚህ ቃል ከለከላቸው፤ በሳኦል ላይ አደጋ እንዲያደርሱበትም አልፈቀደላቸውም። ሳኦልም ከዋሻው ወጥቶ ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዳዊት ከዋሻው ወጥቶ ሳኦልን፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” ብሎ ጠራው። ሳኦልም ወደ ኋላው ዞር ባለ ጊዜ፣ ዳዊት ወደ መሬት ጐንበስ ብሎ እጅ ሲነሣው ተመለከተ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ከዚያ ወጥቶ ሳኦልን በመከተል “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” አለው፤ ሳኦልም መለስ ብሎ ዙሪያውን ሲመለከት ዳዊት በመሬት ላይ ለጥ ብሎ እጅ ነሣውና እንዲህ አለው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በዚህ ቃል ሰዎቹን ከለከላቸው። በሳኦልም ላይ ተነሥተው ይገድሉት ዘንድ አልፈቀደላቸውም፤ ሳኦልም ከዋሻው ተነሥቶ መንገዱን ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም በኋላ ዳዊት ደግሞ ተነሣ፥ ከዋሻውም ወጣ፥ ከሳኦልም በኋላ፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ብሎ ጮኸ፥ ሳኦልም ወደ ኋላው ተመለከተ፥ ዳዊትም ወደ ምድር ተጎንብሶ እጅ ነሣ። |
ልጁ ከሄደ በኋላ፥ ዳዊት ከድንጋዩ በስተ ደቡብ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ በዮናታን ፊት ሦስት ጊዜ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደለት፤ ከዚያም ተሳሳሙ፤ ተላቀሱም፤ በይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር።
ለሰዎቹም፥ “ጌታ በቀባው በጌታዬ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ከማድረግና ጌታ የቀባው ስለ ሆነም እጄን በእርሱ ላይ ከማንሣት ጌታ ይጠብቀኝ” አላቸው።
ከዚያም ዳዊት ከዋሻው ወጥቶ ሳኦልን፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” ብሎ ጠራው። ሳኦልም ወደ ኋላው ዞር ባለ ጊዜ፥ ዳዊት ወደ መሬት ጐንበስ ብሎ እጅ ሲነሣው ተመለከተ፤
ሳኦል የዳዊትን ድምፅ ለይቶ ስላወቀ፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ በእርግጥ የአንተ ድምፅ ነውን?” አለው። ዳዊትም፥ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ አዎን ድምፄ ነው” ሲል መለሰ፤
እርሱም፥ “መልኩ ምን ይመስላል?” ሲል ጠየቃት። እርሷም፥ “ካባ የለበሰ አንድ ሽማግሌ ሰው እየወጣ ነው” አለችው። ሳኦልም ሴትዮዋ ያየችው ሳሙኤል መሆኑን ዐወቀ፤ በመሬትም ላይ ተደፍቶ እጅ ነሣ።