La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 24:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የዳዊት ሰዎችም ዳዊትን፥ “ጌታ፥ ‘የወደድኸውን ታደርግበት ዘንድ ጠላትህን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ’ ብሎ ለአንተ የተናገረው ቀን ዛሬ ነው” አሉት። ዳዊትም በልቡ እየተሳበ ሄዶ የሳኦልን ልብስ ጫፍ ማንም ሳያውቅ ቆርጦ ወሰደ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዳዊት የሳኦልን ልብስ ጫፍ በመቍረጡ ልቡ በሐዘን ተመታ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ዳዊትን የኅሊና ወቀሳ አስጨነቀው፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የዳ​ዊ​ትም ሰዎች፥ “እነሆ፥ ጠላ​ት​ህን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ በዐ​ይ​ን​ህም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህን ታደ​ር​ግ​በ​ታ​ለህ ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የነ​ገ​ረህ ቀን እነሆ ዛሬ ነው” አሉት። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ የሳ​ኦ​ልን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ዘርፍ በቀ​ስታ ቈረጠ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከዚያም በኋላ እንዲህ ሆነ፥ የሳኦልን የልብሱን ዘርፍ ስለቆረጠ የዳዊት ልብ በኅዘን ተመታ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 24:5
6 Referencias Cruzadas  

ታዲያ በፊቱ ክፉ ነገር በማድረግ፥ የጌታን ቃል ያቃለልኸው ስለምንድን ነው? ሒታዊውን ኦርዮን በሰይፍ መታህ፤ ሚስት እንድትሆንህም ሚስቱን ወሰድሃት፤ እርሱንም በአሞናውያን ሰይፍ ገደልኸው።


ዳዊት ሕዝቡን ከቆጠረ በኋላ ኅሊናው ወቀሰው፤ ዳዊትም ጌታን፥ “ባደረግሁት ነገር የፈጸምኩት ታላቅ ኃጢአት ነው፤ አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን በደል ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ የፈጸምኩት ታላቅ የሞኝነት ሥራ ነውና” አለ።


ይህችን ቦታና ሕዝብዋን የተረገሙና ባድማ እንደማደርግ የተናገርኩትን ቃል በሰማህ ጊዜ ልብህ ተነክቶ ራስህን በማዋረድ፥ ልብስህን በመቅደድና በፊቴም በማልቀስህ ጸሎትህን ሰምቼአለሁ።


የአምላኬ ቸርነቱ ይገናኘኛል አምላኬ በጠላቶቼ ላይ ያሳየኛል።


አቢሳም ዳዊትን፥ “ዛሬ እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ ላይ ጥሎታል፤ አሁንም እኔ አንድ ጊዜ በጦር ወግቼ ከመሬት ጋር ላጣብቀው፤ መድገምም አያስፈልገኝም” አለው።