La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 23:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የዚፍ ሰዎች ወደ ጊብዓ ወደ ሳኦል ወጥተው፦ “እነሆ፤ ዳዊት ከየሴሞን በስተ ደቡብ በሐኪላ ኰረብታ ላይ በሖሬሽ ምሽጎች ውስጥ በመካከላችን ተደብቆ ይገኛል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የዚፍ ሰዎች ወደ ጊብዓ ወደ ሳኦል ወጥተው እንዲህ አሉ፤ “እነሆ፤ ዳዊት ከየሴሞን በስተ ደቡብ በኤኬላ ኰረብታ ላይ በሖሬሽ ምሽጎች ውስጥ በመካከላችን ተደብቆ የለምን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚፍ ነዋሪዎች አንዳንዶቹ በጊብዓ ወደሚገኘው ወደ ሳኦል ሄደው እንዲህ አሉ፥ “ዳዊት በእኛ ግዛት ውስጥ ከይሁዳ ምድረ በዳ በስተ ደቡብ ባለው በሐኪላ ተራራ ላይ በምትገኘው በሖሬሽ ተሸሽጎ ይገኛል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የዚፍ ሰዎ​ችም ከአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ወደ ሳኦል ወደ ኮረ​ብ​ታው ወጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “እነሆ፥ ዳዊት በየ​ሴ​ሞን ቀኝ በጠ​ባቡ በኩል በኤ​ኬላ ኮረ​ብታ ላይ በቄኒ ውስጥ በማ​ሴ​ሬት በእኛ ዘንድ ተሸ​ሽጎ የለ​ምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የዚፍ ሰዎችም ወደ ሳኦል ወደ ጊብዓ መጥተው፦ እነሆ፥ ዳዊት በየሴሞን ደቡብ በኩል በኤኬላ ኮረብታ ላይ በጥሻ ውስጥ ባሉት አምባዎች በእኛ ዘንድ ተሸሽጎ የለምን?

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 23:19
6 Referencias Cruzadas  

አስተዳዳሪ ለሐሰተኛ ነገር ትኩረት ቢሰጥ፥ ከእርሱ በታች ያሉት ሁሉ ዓመፀኞች ይሆናሉ።


ዳዊትም ከዚያ ወደ ላይ ወጥቶ በዔንገዲ ምሽጎች ተቀመጠ።


የዚፍ ሰዎችም ወደ ጊብዓ ወደ ሳኦል መጥተው፦ “እነሆ፥ ዳዊት በየሴሞን ፊት ለፊት ባለው በሐኪላ ኮረብታ ላይ ተሸሽጓል” አሉት።


ሳኦልም በየሴሞን ትይዩ በሚገኘው በሐኪላ ኰረብታ ላይ በመንገድ ዳር ሰፈረ፤ ዳዊት ግን በምድረ በዳ ነበር። ዳዊትም ሳኦል እዚያ ድረስ እንደ ተከተለው ባወቀ ጊዜ፥