መልካም የሆነችው የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ እንደሆነችና ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። እነርሱም፦ “እንነሣና እንሥራ” አሉ። ለመልካም ሥራ እጃቸውን አበረቱ።
1 ሳሙኤል 23:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳኦል ልጅ ዮናታንም ዳዊት ወዳለበት ወደ ሖሬሽ ሄዶ፥ በእግዚአብሔር ስም አበረታታው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳኦል ልጅ ዮናታንም ዳዊት ወዳለበት ወደ ሖሬሽ ሄዶ፣ በእግዚአብሔር ስም አበረታታው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሳኦል ልጅ ዮናታንም እዚያው ድረስ ወደ ዳዊት ሄዶ እግዚአብሔር በአስተማማኝ ሁኔታ የሚጠብቀው መሆኑን በመግለጥ እንዲህ እያለ አበረታታው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳኦልም ልጅ ዮናታን ተነሥቶ ወደ ዳዊት ወደ ቄኒ ሄደ። እጁንም በእግዚአብሔር አጸና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳኦልም ልጅ ዮናታን ተነሥቶ ወደ ዳዊት ወደ ጥሻው ውስጥ ሄደ፥ እጁንም በእግዚአብሔር አጽንቶ፦ |
መልካም የሆነችው የአምላኬ እጅ በእኔ ላይ እንደሆነችና ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። እነርሱም፦ “እንነሣና እንሥራ” አሉ። ለመልካም ሥራ እጃቸውን አበረቱ።
ምክንያቱም እኔ ያላሳዘንሁትን የጻድቁን ልብ በውሸት አሳዝናችኋልና፥ ከክፉ መንገዱ ተመልሶ በሕይወትም እንዳይኖር የኃጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና፤
ሰዎቹ ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ነፍሳቸው ተማርራ ሊወግሩት ስለ ተመካከሩ ዳዊት በጣም ተጨነቀ፤ ነገር ግን ዳዊት በአምላኩ በጌታ በረታ።