La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 20:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ የዳዊትን ጠላቶች ሁሉ ከምድረ ገጽ በሚደመስስበት ጊዜ እንኳ፥ ታማኝነትህ ከቤተሰቤ በፍጹም አይቋረጥ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር የዳዊትን ጠላቶች ሁሉ ከምድረ ገጽ በሚደመስስበት ጊዜ እንኳ የበጎነት ሥራህ ከቤተ ሰቤ በፍጹም አይቋረጥ።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ብሞ​ትም ቸር​ነ​ት​ህን እስከ ዘለ​ዓ​ለም ከቤቴ አት​ተው፤ ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳ​ዊ​ትን ጠላ​ቶች ሁሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ከም​ድር ፊት ባጠ​ፋ​ቸው ጊዜ የዮ​ና​ታን ስም በዳ​ዊት ቤት ይገ​ኛል።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ደግሞም እግዚአብሔር የዳዊትን ጠላቶች ሁሉ እያንዳንዱ ከምድር ባጠፋቸው ጊዜ ለዘላለም ቸርነትህን ከቤቴ አታርቀው።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 20:15
7 Referencias Cruzadas  

እንግዲህ፥ በጎ ነገር በገጠመህ ጊዜ፥ እኔን አስበህ ቸርነት አድርግልኝ፤ ስለ እኔም ለፈርዖን ንገርልኝ፤ ከዚህም እስር ቤት አስወጣኝ፤


ንጉሥ ዳዊት በራሱና በሳኦል ልጅ በዮናታን መካከል በጌታ ፊት ስላደረጉት መሐላ ሲል የሳኦልን ልጅ፥ የዮናታንን ልጅ መፊቦሼትን ከሞት አተረፈ።


እኔም እንዳልሞት፥ በሕይወት እስካለሁ የጌታን ታማኝ ፍቅር አሳየኝ፤


አንተና እኔ ስለ ተነጋገርነው ነገር እነሆ፤ ጌታ በመካከላችን ለዘለዓለም ምስክር ነው።”


ዮናታንም ዳዊትን፤ “ ‘በአንተና በእኔ፥ በዘሮችህና በዘሮቼ መካከል ጌታ ለዘለዓለም ምስክር ነው’ ተባብለን ወዳጅነታችን እንዲጸና በጌታ ስም ስለ ተማማልን እንግዲህ በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፤ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።


እነሆ፤ አንተ በእርግጥ እንደምትነግሥና የእስራኤል መንግሥት በእጅህ እንደምትጸና ዐውቃለሁ።