1 ሳሙኤል 15:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ሂድ፤ አማሌቃውያንን ውጋ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ አንዱንም አታስቀር፤ ወንዱንም ሴቱንም፥ ልጁንም ሕፃኑንም፥ የቀንድ ከብቱንም በጉንም፥ ግመሉንም አህያውንም ግደል።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ሂድ፤ አማሌቃውያንን ውጋ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ አንዱንም አታስቀር፤ ወንዱንና ሴቱን፣ ልጁንና ሕፃኑን፣ የቀንድ ከብቱንና በጉን፣ ግመሉንና አህያውን ግደል።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሄደህ በዐማሌቃውያን ላይ አደጋ በመጣል ያላቸውን ሁሉ ደምስስ፤ ከእነርሱ ምንም ነገር አታስቀር፤ ወንዶችን፥ ሴቶችን፥ ልጆችንና ሕፃናትን፥ ከብቶችን፥ በጎችን፥ ግመሎችንና አህዮችን ሁሉ ግደል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ሄደህ አማሌቅንና ኢያሬምን ምታ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ ከእነርሱም የምታድነው የለም። አጥፋቸው፤ መከራም አጽናባቸው፤ የእነርሱ የሆነውን ሁሉ አጥፋ፤ ለያቸውም፤ አትማራቸውም፤ ወንዱንና ሴቱን፥ ብላቴናውንና ሕፃኑን፥ በሬውንና በጉን፥ ግመሉንና አህያውን ግደል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፥ አትማራቸውም፥ ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕፃኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል። |
ጌታም ሙሴን፦ “ይህንን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፥ በኢያሱም ጆሮ አኑረው፥ የአማሌቅን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና” አለው።
አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥
በለዓምም አማሌቅን አይቶ ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “የአሕዛብ መጀመሪያ የሆነ አማሌቅ ነበረ፤ ፍጻሜው ግን ወደ ጥፋት የሚያመራ ይሆናል።”
እርሷንም ንጉሥዋንም ከተሞችዋንም ሁሉ ያዙ፤ በሰይፍም ስለት መቱአቸው፥ በእነርሱም ውስጥ ያሉትን ሰዎች ሁሉ ፈጽመው አጠፉ፤ ማንንም አላስቀረም፤ በኬብሮን፥ ደግሞ በልብናና በንጉሥዋ እንዳደረገው እንዲሁ በዳቤርና በንጉሥዋ አደረገ።
ነገር ግን ሳኦልና ሠራዊቱ አጋግን፥ ምርጥ ምርጡን በግና የቀንድ ከብት፥ የሰባውን ጥጃና ጠቦት፥ መልካም የሆነውን ሁሉ ሳይገድሉ ተውት። እነዚህን ፈጽመው ለማጥፋት ፈቃደኞች አልነበሩም፤ ነገር ግን የተናቀውንና የማይጠቅመውን ሁሉ አጠፉ።
የካህናቱንም ከተማ ኖብን በሰይፍ መታት፥ በዚያ የሚኖሩትንም ወንዶችንና ሴቶችን፥ ልጆችንና ጡት የሚጠቡ ሕፃናትን፥ እንዲሁም በሬዎችንና አህያዎችን፥ በጎችንም ሁሉ በሰይፍ ስለት አስገደለ።
ዳዊትም ምድሪቱን በመታበት ጊዜ፥ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አላስቀረም፤ በጎችንና ላሞችን፥ አህዮችንና ግመሎችን እንዲሁም ልብሶችን ወሰደ፤ ወደ አኪሽም ይዞ ተመለሰ።
ዳዊት፥ ከዚያች እለት ምሽት ጀምሮ እስከ ማግሥቱ ምሽት ድረስ ወጋቸው፤ በግመል ተቀምጠው ከሸሹት አራት መቶ ወጣቶች በስተቀር፥ ከመካከላቸው ያመለጠ አንድም አልነበረም።