ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎች ከእስራኤል መረጠ፤ ሁለቱ ሺህ በማክማስና በተራራማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋር፥ አንዱ ሺህ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋር ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ ድንኳኖቻቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።
1 ሳሙኤል 13:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ ሳሙኤል ከጌልገላ ተነሥቶ በብንያም ግዛት ወዳለው ወደ ጊብዓ ሄደ። ሳኦልም አብረውት የነበሩትን ሰዎች ቆጠራቸው፤ ስድስት መቶ ያህል ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ በኋላ ሳሙኤል ከጌልገላ ተነሥቶ በብንያም ግዛት ወዳለው ወደ ጊብዓ ወጣ። ሳኦልም ዐብረውት የነበሩትን ሰዎች ቈጠራቸው፤ ብዛታቸውም ስድስት መቶ ያህል ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤልም ከጌልጌላ ተነሥቶ ሄደ፤ ሳኦልም ከወታደሮቹ ጋር ለመደባለቅ ሲሄድ የቀሩት ሰዎች ተከተሉት፤ ከጌልገላም ተነሥተው በብንያም ግዛት ወደምትገኘው ወደ ጊብዓ ሄዱ፤ ሳኦልም ሠራዊቱን በቈጠረ ጊዜ ብዛታቸው ስድስት መቶ ሆኖ ተገኘ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ከጌልጌላ ተነሥቶ መንገዱን ሄደ፤ የቀሩትም ሕዝብ ሳኦልን ተከትለው ሰልፈኞቹን ሊገናኙ ሄዱ። ከጌልጌላም ተነሥተው ወደ ብንያም ገባዖን መጡ፤ ሳኦልም ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ቈጠረ፤ ስድስት መቶም የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ከጌልገላ ተነሥቶ መንገዱን ሄደ፥ የቀሩትም ሕዝብ ሳኦልን ተከትለው ሰልፈኞቹን ሊገናኙ ሄዱ። ከጌልገላም ተነሥተው ወደ ብንያም ጊብዓ መጡ፥ ሳኦልም ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሕዝብ ቆጠረ፥ ስድስት መቶም የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ። |
ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎች ከእስራኤል መረጠ፤ ሁለቱ ሺህ በማክማስና በተራራማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋር፥ አንዱ ሺህ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋር ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ ድንኳኖቻቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።
ሳሙኤልም ጠዋት ተነሥቶ በማለዳ ሳኦልን ለመገናኘት ሄደ፤ ነገር ግን፥ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ ሄዷል፤ ለራሱ ክብር የመታሰቢያ ሐውልት በዚያ ካቆመ በኋላ ተመልሶ ወደ ጌልገላ ወርዷል” ተብሎ ተነገረው።