1 ሳሙኤል 12:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክፉ ሥራችሁ ብትጸኑ ግን፥ እናንተም ንጉሣችሁም ትጠፋላችሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በክፉ ሥራችሁ ብትጸኑ ግን፣ እናንተም ንጉሣችሁም ትጠፋላችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአት በመሥራት ብትጸኑ ግን እናንተም ንጉሣችሁም ትጠፋላችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ክፉ ብትሠሩ እናንተም፥ ንጉሣችሁም ትጠፋላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ክፉ ብትሠሩ እናንተም ንጉሣችሁም ትጠፋላችሁ። |
“ጌታ አንተን በአንተም ላይ የምታነግሠውን ንጉሥ አንተና አባቶችህ ወደማታውቁት ሕዝብ ይወስዳችኋል። በዚያም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማልክትን ታመልካለህ።
ጌታ አምላክህንም ብትረሳና፥ ባዕዳን አማልክት ብትከተል ብታመልካቸውም ብትሰግድላቸውም፥ ፈጽሞ እንደምትጠፉ ዛሬውኑ አበክሬ አስጠነቅቅሃለሁ።
ጌታ አምላካችሁ ያዘዛችሁን ቃል ኪዳን ስታፈርሱ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ስታመልኩ፥ ስትሰግዱላቸውም፥ በዚያ ጊዜ የጌታ ቁጣ ይነድድባችኋል፥ ከሰጣችሁም ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።”