La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 10:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያ ነዋሪ የሆነ አንድ ሰው፥ “አባታቸውስ ማን ነው?” ብሎ መለሰ። ስለዚህ፥ “ሳኦልም ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል ምሳሌያዊ አነጋገር ሆነ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያ ነዋሪ የሆነ አንድ ሰው፣ “የእነርሱስ አባት ማን ነው?” ብሎ መለሰ። ስለዚህ፣ “ሳኦልም ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል ምሳሌያዊ አነጋገር ሆነ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያም የሚኖር አንድ ሰው “የእነዚህስ የሌሎቹ ነቢያት ሁኔታ እንዴት ነው? አባቶቻቸውስ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቀ፤ “ሳኦልም ደግሞ ከነቢያት ወገን ነውን?” የሚል የምሳሌ አነጋገር የመነጨውም ከዚህ ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከዚ​ያም ስፍራ ያለ አንድ ሰው፥ “አባ​ቱስ ማን ነው?” ብሎ መለሰ። ስለ​ዚ​ህም “ሳኦል ደግሞ ከነ​ቢ​ያት ወገን ነውን?” የሚል ምሳሌ ሆነ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከዚያም ስፍራ ያለ አንድ ሰው፦ አባታቸውስ ማን ነው? ብሎ መለሰ። ስለዚህም፦ ሳኦል ደግሞ ከነቢያት ወገን ነውን? የሚል ምሳሌ ሆነ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 10:12
7 Referencias Cruzadas  

ልጆችሽም ሁሉ ከጌታ የተማሩ ይሆናሉ፥ የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል።


‘ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፤’ ተብሎ በነቢያት ተጽፎአል፤ እንግዲህ ከአብ የሰማና የተማረ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል።


ስለዚህም ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ትምህርቴስ የላከኝ ነው እንጂ የእኔ አይደለም፤


መልካም ስጦታ ሁሉ፥ ፍጹምም በረከት ሁሉ፥ እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከላይ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


ሳኦል ትንቢት መናገሩን ከፈጸመ በኋላ ወደ ማምለኪያው ኰረብታ ሄደ።


ስለዚህ ሳኦል በራማ ወደምትገኘው ወደ የራማዋ ናዮት ሄደ፤ ሲሄድ ሳለም የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱም ላይ ደግሞ ወረደ፤ ወደ ናዮት እስኪደርስ ድረስም ትንቢት እየተናገረ ተጓዘ።


እርሱም ልብሱን አውልቆ፥ በሳሙኤልም ፊት ደግሞ ትንቢት ተናገረ፤ በዚህ ሁኔታም ቀኑንና ሌሊቱን በሙሉ ራቁቱን ተጋደመ። ሕዝቡ፥ “ሳኦልም ደግሞ ከነቢያት እንደ አንዱ ሆኖ ተቆጠረ?” ካለው የተነሣ ነው።