La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 1:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ ማሕፀኗን ስለዘጋም ጣውንቷ ሆን ብላ ታስቆጣት፥ ታበሳጫትም ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ማሕፀኗን ስለ ዘጋም ጣውንቷ ታስቈጣት፣ ታበሳጫትም ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርም ልጅ ስላልሰጣት ጣውንትዋ ጵኒና ሐናን የሚያስቈጣ ነገር በመፈለግ ታበሳጫት ነበር፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እንደ መከ​ራ​ዋና እንደ ኀዘ​ን​ዋም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ አል​ሰ​ጣ​ትም ነበር። ስለ​ዚ​ህም ታዝን ነበር። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​ፀ​ን​ዋን ዘግ​ት​ዋ​ልና፥ ልጆ​ች​ንም አል​ሰ​ጣ​ት​ምና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር ግን ማኅፀንዋን ዘግቶ ነበርና ጣውንትዋ ታስቆጣት ታበሳጫትም ነበር።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 1:6
8 Referencias Cruzadas  

ራሔልም ለያዕቆብ ልጆችን እንዳልወለደች ባየች ጊዜ በእኅትዋ ቀናችባት፥ ያዕቆብንም፦ ልጆች ስጠኝ፥ ይህስ ካልሆነ እሞታለሁ አለችው።


የሳኦልም ልጅ ሜልኮል እሰከሞተችበት ጊዜ ድረስ ልጅ አልወለደችም ነበር።


“የማትወልደውን መካኒቱን ይበድላታል፥ ለመበለቲቱም መልካም አያደርግም።


“ቸርነትን ለወዳጁ የሚነፍግ፥ ሁሉን ቻይ አምላክን መፍራት የተወ ነው።


እኅትዋ በሕይወት እስካለች ድረስ ኃፍረተ ሥጋዋን ለመግለጥ የእርሷን እኅት እንደ ሁለተኛ ሚስት አድርገህ አታግባ።


ነገር ግን አንድ ነገር ብቻ እንድትፈቅድልኝ እለምንሃለሁ፤ ከእንግዲህ ባል ስለማላገባ ከባልንጀሮቼ ጋር ወደ ተራሮች ወጥቼ እየዞርሁ ሁለት ወር እንዳለቅስ አሰናብተኝ።”


ወደ ጌታ ቤት በምትወጣበት ጊዜ ሁሉ ይህ በየዓመቱ ይደጋገም ነበር፤ እስክታለቅስና መብላት እስኪያቅታት ድረስ ታበሳጫት ነበር።


ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፦ “ልቤ በጌታ ደስ ይለዋል፥ ቀንዴም በጌታ ከፍ ከፍ ብሏል፤ በማዳንህ ደስ ብሎኛልና፥ አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ።