ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመት ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር።
1 ነገሥት 9:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን በኤዶም ምድር በቀይ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው በኤላት አጠገብ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦችን ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ንጉሡ ሰሎሞን በኤዶም ምድር የባሕር ጠረፍ፣ በኤላት አጠገብ፣ በቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦችን ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን በኤዶም ምድር በቀይ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው በኤላት አጠገብ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦችን ሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ሰሎሞን በኤዶምያስ ምድር በኤርትራ ባሕር ዳር በኤላት አጠገብ ባለችው በጋሴዎንጋቤር መርከቦችን ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሰሎሞን በኤዶምያስ ምድር በኤርትራ ባሕር ዳር በኤሎት አጠገብ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦች ሠራ። |
ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመት ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር።
ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ውቅያኖስን አቋርጠው ከኦፊር ወርቅ የሚያመጡለትን የተርሴስን ዓይነት መርከቦች አሠርቶ ነበር፤ ነገር ግን መርከቦቹ በኤጽዮንጋብር ወደብ ላይ ስለ ተሰበሩ መጓዝ አልቻሉም።
“እኛም ወንድሞቻችን የዔሳው ልጆች ከተቀመጡት ሴይር አልፈን፥ በዓረባ መንገድ ከኤላትና ከዔጽዮንጋብር አለፍን። ተመልሰንም በሞዓብ ምድረ በዳ መንገድ አለፍን።