ድምፁንም ከፍ በማድረግ በዚያ ተሰብስቦ በነበረው ሕዝብ ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር በረከት እንዲወርድ እንዲህ ሲል ጸለየ፤
ከዚያም ቆሞ መላውን የእስራኤልን ጉባኤ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ ሲል መረቀ፤
ቆሞም የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ በታላቅ ድምፅ ሲመርቅ እንዲህ አለ፦
ቆሞም የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ በታላቅ ድምጽ ሲመርቅ እንዲህ አለ
ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ ሕዝቡን በሠራዊት ጌታ ስም ባረከ።
ንጉሥ ሰሎሞንም የእስራኤል ጉባኤ በዚያ ቆመው ሳሉ፥ ወደ እነርሱ ፊቱን ዞር አድርጎ የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ ባረከ።
ዳዊትም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕት አቅርቦ በፈጸመ ጊዜ በጌታ ስም ሕዝቡን ባረከ።
ሕዝቅያስና ሹማምንቱም መጥተው ክምሩን ባዩ ጊዜ ጌታንና ሕዝቡን እስራኤልን ባረኩ።
ሙሴም ሥራውን ሁሉ አየ፥ እነሆ ልክ ጌታ እንዳዘዘው አድርገውት ነበር፤ እንዲሁ አድርገውት ነበር፤ ሙሴም ባረካቸው።