1 ነገሥት 7:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤቱ ከምሰ ሶዎቹ ላይ ያረፉ አግዳሚ ተሸካሚዎች አሉት፤ በእያንዳንዱ ዐምድ ላይ ዐሥራ አምስት፥ በድምሩ አርባ አምስት ተሸጋጋሪዎች ሲኖሩ፥ ከእነዚህም ተሸጋጋሪዎች በላይ ከዝግባ የተሠራ የጣሪያ ክዳን ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤቱ ከምሰሶዎቹ ላይ ያረፉ አግዳሚ ተሸካሚዎች አሉት፤ በእያንዳንዱ ዐምድ ላይ ዐሥራ ዐምስት፣ በድምሩ አርባ ዐምስት ተሸጋጋሪዎች ሲኖሩ፣ ከእነዚህም ተሸጋጋሪዎች በላይ ከዝግባ የተሠራ የጣሪያ ክዳን ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአዕማዱም ላይ በነበሩ አግዳሚዎች ቤቱ በዋንዛ ሳንቃ ተሸፍኖ ነበር፤ አዕማዱም በአንዱ ወገን ዐሥራ አምስት፥ በአንዱ ወገን ዐሥራ አምስት የሆኑ አርባ አምስት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአዕማዱም ላይ በነበሩ አግዳሚዎች ቤቱ በዝግባ ሳንቃ ተሸፍኖ ነበር፤ አዕማዱም በአንዱ ተራ ዐሥራ አምስት፥ በአንዱ ተራ ዐሥራ አምስት እየሆኑ አርባ አምስት ነበሩ። |
የሊባኖስ ዱር የተባለ ቤተ መንግሥት ሠራ፤ ይህም ርዝመቱ መቶ ክንድ፥ ወርዱ አምሳ ክንድ፥ ቁመቱ ሠላሳ ክንድ ሲሆን፥ በአራት ረድፍ የቆሙ የዝግባ ምሰሶዎች ደግፈው የያዟቸው አግዳሚ የዝግባ ተሸካሚዎች ነበሩት።