ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ።
1 ነገሥት 4:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤንዴቀር፦ የማቃጽ፥ የሻዓልቢም፥ የቤትሼሜሽ፥ የኤሎንና የቤት ሐናን ከተሞች ገዥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤንጼቄር፣ በማቃጽ፣ በሻዓልቢም፣ በቤትሳሚስ፣ በኤሎንቤትሐናን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤንዴቀር፦ የማቃጽ፥ የሻዓልቢም፥ የቤትሼሜሽ፥ የኤሎንና የቤት ሐናን ከተሞች ገዥ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማኪስና በሰአልቢን፥ በቤት ሳሚስና በኤሎንቤትሐናን የዴቀር ልጅ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማቃጽና በሸዓልቢም በቤትሳሚስና በኤሎንቤትሐና የዴቀር ልጅ፤ |
ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ።
ከዚያም ላሞቹ መንገዳቸውን በመያዝ፥ እምቧ እያሉ፥ ቀጥ ብለው ወደ ቤትሼሜሽ አመሩ። የፍልስጥኤም ገዢዎችም እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ተከተሏቸው።
ከዚያም ወዴት እንደሚሄድ ተመልከቱ፤ ወደ ገዛ አገሩ ወደ ቤትሼሜሽ አቅጣጫ የሚሄድ ከሆነ፥ ይህን ታላቅ መከራ ያመጣብን እርሱ ነው። ወደዚያ ካልሄደ ግን፥ መከራው በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የእርሱ እጅ እንዳልመታን እናውቃለን።”