La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 20:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አክዓብም “ግንባር ቀደም ሆኖ የሚዘምተው ማን ይሁን?” ሲል ጠየቀ። ነቢዩም “ጌታ ‘በአውራጃ አስተዳዳሪዎች የሚታዘዙ ወጣትነት ያላቸው ወታደሮች ግንባር ቀደም ሆነው ይዝመቱ’ ይላል” አለው፤ ንጉሡም “ጦርነቱን ማን ይጀምር” ሲል ጠየቀ፤ ነቢዩም “አንተ ራስህ ጀምር” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አክዓብም፣ “ይህን የሚያደርገው ማን ነው?” ሲል ጠየቀ። ነቢዩም፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ይህን የሚያደርጉት የየአውራጃው አዛዥ የሆኑ ወጣት መኰንኖች ናቸው’ ” አለው። “ታዲያ ጦርነቱን የሚጀምረው ማን ነው?” ሲል ጠየቀ። ነቢዩም፣ “አንተው ትጀምራለህ” ብሎ መለሰ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አክዓብም “ግንባር ቀደም ሆኖ የሚዘምተው ማን ይሁን?” ሲል ጠየቀ። ነቢዩም “እግዚአብሔር ‘በአውራጃ አስተዳዳሪዎች የሚታዘዙ ወጣትነት ያላቸው ወታደሮች ግንባር ቀደም ሆነው ይዝመቱ’ ይላል” አለው፤ ንጉሡም “ጦርነቱን ማ ይጀምር” ሲል ጠየቀ። ነቢዩም “አንተ ራስህ ጀምር” አለው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ኤል​ዛ​ቤ​ልም፥ “ናቡቴ በድ​ን​ጋይ ተደ​ብ​ድቦ ሞተ” ብለው ላኩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ኤልዛቤልም “ናቡቴ ተወግሮ ሞተ፤” ብለው ላኩ።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 20:14
8 Referencias Cruzadas  

በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ “ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ” አለው። ኤልያስም “ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ‘ዝናቡ ሳያቋርጥህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ’ ብለህ ንገረው” ሲል አዘዘው።


በዚህን ጊዜ አንድ ነቢይ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “ጌታ ‘ከቤንሀዳድ ሠራዊት ብዛት የተነሣ አትፍራ! እኔ ዛሬ በዚህ ሠራዊት ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አደርጋለሁ፤ አንተም ደግሞ እኔ ጌታ መሆኔን ታውቃለህ’ ይልሃል” አለው።


ስለዚህ ንጉሡ ብዛታቸው ሁለት መቶ ሠላሳ ሁለት ብቻ የሆነ በአውራጃ አስተዳዳሪዎች ትእዛዝ ሥር የሆኑትን ወጣትነት ያላቸውን ወታደሮች ጠራ፤ ቀጥሎም ጠቅላላ ብዛቱ ሰባት ሺህ የሆነ የእስራኤልን ሠራዊት ጠራ።


ወጣቶቹም ወታደሮች ግንባር ቀደም ሆነው ወደ ፊት አመሩ፤ ቤንሀዳድ ልኮአቸው የነበሩትም ቃፊሮች “አንድ የወታደሮች ቡድን ከሰማርያ ወጥቶ ወደዚህ እየመጣ ነው” ብለው ነገሩት።


በዚህ ሁኔታ ዳዊት በወንጭፍና በድንጋይ ብቻ ፍልስጥኤማዊውን አሸነፈው፤ በእጁም ሰይፍ ሳይዝ ፍልስጥኤማዊውን መታው፤ ገደለውም።