1 ነገሥት 2:46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ሺምዒን እንዲገድል ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ ሺምዒን ገደለው፤ በዚህም ዓይነት መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ የጸና ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንጉሡ የዮዳሄን ልጅ በናያስን አዘዘው፤ በናያስም ወጣ፤ ሳሚንም መትቶ ገደለው። በዚህ ጊዜም መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ ጸና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ለዮዳሄ ልጅ ለበናያ ሺምዒን እንዲገድል ትእዛዝ አስተላለፈ፤ በናያም ሄዶ ሺምዒን ገደለው፤ በዚህም ዐይነት መንግሥቱ በሰሎሞን እጅ የጸና ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰሎሞንም የዮዳሄን ልጅ በንያስን አዘዘው፤ ወጥቶም ገደለው። የሰሎሞንም መንግሥት በኢየሩሳሌም ጸና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም የዮዳሄን ልጅ በናያስን አዘዘው፤ ወጥቶም ወደቀበት፤ ሞተም። መንግሥትም በሰሎሞን እጅ ጸና። |