በዚያም ዘመን እግዚአብሔር የእስራኤል ግዛት ስፋቱ እንዲቀነስ ማድረግ ጀመረ፤ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል እስራኤልን ድል ነሥቶ የእስራኤልን ግዛት ሁሉ ያዘ።
1 ነገሥት 19:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአዛሄል እጅ ከመገደል ተርፎ የሚያመልጠውን ማንኛውንም ሰው ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩ እጅ የሚያመልጠውንም ኤልሳዕ ይገድለዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአዛሄል ሰይፍ ያመለጠውን ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩ ሰይፍ ያመለጠውን ደግሞ ኤልሳዕ ይገድለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአዛሄል እጅ ከመገደል ተርፎ የሚያመልጠውን ማንኛውንም ሰው ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩ እጅ የሚያመልጠውንም ኤልሳዕ ይገድለዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአዛሄልም ሰይፍ የሚያመልጠውን ሁሉ ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩም ሰይፍ የሚያመልጠውን ሁሉ ኤልሳዕ ይገድለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአዛሄልም ሰይፍ ያመለጠውን ሁሉ፥ ኢዩ ይገድለዋል፤ ከኢዩም ሰይፍ ያመለጠውን ሁሉ ኤልሳዕ ይገድለዋል። |
በዚያም ዘመን እግዚአብሔር የእስራኤል ግዛት ስፋቱ እንዲቀነስ ማድረግ ጀመረ፤ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል እስራኤልን ድል ነሥቶ የእስራኤልን ግዛት ሁሉ ያዘ።
አዛሄልም “ጌታዬ ስለምን ታለቅሳለህ?” ሲል ጠየቀው። ኤልሳዕም “በእስራኤል ሕዝብ ላይ የምትፈጽመውን አሠቃቂ ነገር ስለማውቅ ነው፤ ምሽጎቻቸውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ምርጥ የሆኑ ወጣቶቻቸውን ታርዳለህ፤ ሕፃናታቸውን በድንጋይ ላይ ትፈጠፍጣለህ፤ እርጉዞች የሆኑ ሴቶቻቸውንም ሆድ ትሰነጥቃለህ” ሲል መለሰለት።
ባለሟሎቹ ከሆኑት ባለ ሥልጣኖች አንዱ የሆነውን አዛሄልን ጠርቶ፥ “ለነቢዩ ስጦታ ይዘህ ሂድና እኔ ከዚህ በሽታ እድን ወይም አልድን እንደሆነ እግዚአብሔርን እንዲጠይቅልኝ ለምነው” አለው።
ስለዚህ የናሜሲ የልጅ ልጅ፥ የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዩ በኢዮራም ላይ አሤረ። በዚህ ጊዜ ኢዮራምና እስራኤል ሁሉ በሬማት የምትገኘውን ገለዓድን ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጥቃት ለማዳን ይጠብቁ ነበር።
“ዘበኛውም እንደገና መልእክተኛው በመምጣት ላይ ወዳለው ጭፍራ ደርሶአል፤ ነገር ግን ተመልሶ አልመጣም” ካለ በኋላ “የጭፍራው መሪ ሠረገላ አነዳዱ እንደ እብድ ሰው ነው! እንዲያውም ልክ ኢዩን ይመስላል!” ሲል ተናገረ።
ኢዩ ቀስቱን ስቦ ባለው ኃይል በመጠቀም ፍላጻውን ባስፈነጠረ ጊዜ ኢዮራምን ወግቶ በትከሻዎቹ መካከል እስከ ልቡ ዘለቀ፤ ኢዮራምም ሞቶ በሠረገላው ውስጥ ወደቀ።
ኢዩ ቢድቃር ተብሎ የሚጠራውን የቅርብ ረዳቱን “ሬሳውን አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ ወርውረህ ጣለው፤ እኔና አንተ የንጉሥ ኢዮራም አባት ከነበረው ከአክዓብ በስተ ኋላ እየጋለብን ስንሄድ እግዚአብሔር በአክዓብ ላይ የተናገረውን ቃል አስታውስ፤
ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤ በአፉ በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
በሞዓብ ላይ የመጐብኘትን ዓመት አመጣበታለሁና፥ ይላል ጌታ፤ ከአስፈሪውም ነገር የሸሸ በጉድጓድ ውስጥ ይወድቃል፥ ከጉድጓድም ውስጥ የሚወጣ በወጥመድ ይያዛል።
ፊቴን በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፥ ከእሳት ቢያመልጡም፥ እሳት ግን ይበላቸዋል፥ ፊቴን በእነርሱ ላይ ባደረግሁ ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።