እርሷም ኤልያስን “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ስለምን ይህን አደረግህብኝ? ወደዚህ የመጣኸው ኃጢአቴን አስታውሰህ ልጄ እንዲሞትብኝ ለማድረግ ነውን?” ስትል ጠየቀችው።
1 ነገሥት 17:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልያስም “ልጅሽን ወደ እኔ አምጪው” አላት። ልጁንም ከዕቅፍዋ ወስዶ እርሱ ወደሚኖርበት ሰገነት አውጥቶ በአልጋው ላይ አጋደመው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልያስም መልሶ፣ “ልጅሽን ስጪኝ” አላት፤ ልጁንም ከዕቅፏ ወስዶ እርሱ ወደሚኖርበት ሰገነት በማውጣት በዐልጋው ላይ አስተኛው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልያስም “ልጅሽን ወደ እኔ አምጪው” አላት። ልጁንም ከዕቅፍዋ ወስዶ እርሱ ወደሚኖርበት ሰገነት አውጥቶ በአልጋው ላይ አጋደመው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልያስም፥ “ልጅሽን ስጪኝ” አላት፥ ከብብቷም ወስዶ ተቀምጦበት ወደ ነበረው ሰገነት አወጣው፤ በአልጋውም ላይ አስተኛው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤልያስም “ልጅሽን ስጪኝ፤” አላት። ከብብትዋም ወስዶ ተቀምጦበት ወደ ነበረው ሰገነት አወጣው፤ በአልጋውም ላይ አጋደመው። |
እርሷም ኤልያስን “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ስለምን ይህን አደረግህብኝ? ወደዚህ የመጣኸው ኃጢአቴን አስታውሰህ ልጄ እንዲሞትብኝ ለማድረግ ነውን?” ስትል ጠየቀችው።
ከዚህ በኋላ ኤልያስ ድምፁን ከፍ በማድረግ “ጌታ አምላኬ ሆይ! ስለምን በዚህች ባሏ በሞተባት ሴት ላይ ይህን የመሰለ አሠቃቂ ነገር አደረግህ? እርሷ እኔን በማስተናገድ ታላቅ ቸርነት አድርጋልኛለች፤ ታዲያ አንተ ስለምን ልጇ እንዲሞት አደረግህ?” ሲል ጸለየ።
ስለዚህም በሰገነቱ ላይ አንድ ትንሽ ክፍል ሠርተን በዚያች ውስጥ አንድ አልጋ፥ አንድ ጠረጴዛ፥ አንድ ወንበርና አንድ የፋኖስ መብራት እናኑርለት፤ እርሱም እኛን ለመጐብኘት በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ ማረፊያ ትሆነዋለች።”