መንግሥትንም ከዳዊት ትውልድ ወስጄ ለአንተ ሰጠሁህ፤ ይሁን እንጂ አንተ ለእኔ ፍጹም ታማኝ ሆኖ ትእዛዞቼን እንደ ጠበቀውና እኔ ደስ የምሰኝበትን ነገር ሁሉ ያደርግ እንደነበረው እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ሆነህ አልተገኘህም።
1 ነገሥት 15:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ይህን ያደረገበት ምክንያት ዳዊት በሒታዊው ኦርዮን ላይ ከፈጸመው ኃጢአት በቀር ጌታን ደስ የሚያሰኝ ነገር በማድረጉና ትእዛዙንም በብርቱ ጥንቃቄ በመጠበቁ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት በኬጢያዊው በኦርዮ ላይ ካደረሰው በደል በቀር፣ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አድርጓል፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ፈቀቅ ያለበት ጊዜ አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ይህን ያደረገበት ምክንያት ዳዊት በሒታዊው ኦርዮን ላይ ከፈጸመው ኃጢአት በቀር እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር በማድረጉና ትእዛዙንም በብርቱ ጥንቃቄ በመጠበቁ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኬጥያዊው ከኦርዮ ነገር በቀር ዳዊት በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አድርጎ ነበርና፥ ካዘዘውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላለም ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊት በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አድርጎ ነበርና፥ ካዘዘውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላለም ነበርና። |
መንግሥትንም ከዳዊት ትውልድ ወስጄ ለአንተ ሰጠሁህ፤ ይሁን እንጂ አንተ ለእኔ ፍጹም ታማኝ ሆኖ ትእዛዞቼን እንደ ጠበቀውና እኔ ደስ የምሰኝበትን ነገር ሁሉ ያደርግ እንደነበረው እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ሆነህ አልተገኘህም።
አቢያም፥ እንደ ታላቁ አያቱ እንደ ዳዊት በጌታ ዘንድ ፍጹም ታማኝ ሆኖ በመገኘት ፈንታ፥ አባቱ ሮብዓም ይፈጽመው የነበረውን ኃጢአት ሁሉ መሥራቱን ቀጠለ።
ሰሎሞን ጌታን ይወድ ነበር፤ የአባቱንም የዳዊትን መመሪያ ይጠብቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ እንስሶችን እያረደ በተለያዩ ኰረብቶች ላይ መሥዋዕት ያቀርብ፥ ዕጣንም ያጥን ነበር።
አንተ ግን አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በቅንነትና በታማኝነት እኔን ብታገለግል፥ የእኔን ሕግና ሥርዓት ብትጠብቅ፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብትፈጽም፥
ኢዮስያስ የቀድሞ አባቱን የዳዊትን መልካም ምሳሌነት በመከተልና ለእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ታዛዥ በመሆን፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ።
እርሱንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፤ ሲመሰክርለትም ‘እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ፤’ አለ።
እርሱና ዘሮቹ በእስራኤል ላይ ረጅም ዘመን እንዲገዙ፥ ከሕጉ ቀኝም ግራም አይበል፤ ራሱን ከሌሎች ወንድሞቹ በላይ የተሻለ አድርጎ አይኩራ።”
ጌታዬ የጌታን ጦርነት ስለሚዋጋ ጌታም ለጌታዬ የታመነ ቤት በእርግጥ ለዘለዓለም የሚያጸናለት በመሆኑ፥ እባክህ የእኔን የአገልጋይህን በደል ይቅር በል፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህ።