Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 34:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በጌታም ፊት ቅን ነገር አደረገ፥ በአባቱም በዳዊት መንገድ ሄደ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም፤ በአባቱ በዳዊት መንገድ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ኢዮስያስ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር አደረገ፤ የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን መልካም ምሳሌነት ከመከተል ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት መን​ገድ ሄደ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በእግዚአብሔርም ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ በአባቱም በዳዊት መንገድ ሄደ፤ ወደ ቀኝም፥ ወደ ግራም አላለም።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 34:2
15 Referencias Cruzadas  

አባቱም ዳዊት እንዳደረገ ሁሉ በጌታ ፊት ቅን ነገር አደረገ።


ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፥ እግርህንም ከክፉ መልስ።


በፊተኛይቱ በአባቱ በዳዊት መንገድ ሄዶአልና ጌታም ከኢዮሣፍጥ ጋር ነበረ፤ በኣሊምንም አልፈለገም፥


አሳም በአምላኩ በጌታ ፊት መልካምና ቅን ነገር አደረገ፤


ኢዮስያስ የቀድሞ አባቱን የዳዊትን መልካም ምሳሌነት በመከተልና ለእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ታዛዥ በመሆን፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ።


ጌታ ይህን ያደረገበት ምክንያት ዳዊት በሒታዊው ኦርዮን ላይ ከፈጸመው ኃጢአት በቀር ጌታን ደስ የሚያሰኝ ነገር በማድረጉና ትእዛዙንም በብርቱ ጥንቃቄ በመጠበቁ ነው።


መንግሥትንም ከዳዊት ትውልድ ወስጄ ለአንተ ሰጠሁህ፤ ይሁን እንጂ አንተ ለእኔ ፍጹም ታማኝ ሆኖ ትእዛዞቼን እንደ ጠበቀውና እኔ ደስ የምሰኝበትን ነገር ሁሉ ያደርግ እንደነበረው እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ሆነህ አልተገኘህም።


ስለዚህም በሙሴ ሕግ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ ለመጠበቅና ለማድረግ በጣም በርቱ፥ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ።


ነገር ግን ጽና፥ እጅግም በርታ፤ ባርያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ከእርሱ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።


ሌሎችን አማልክት በመከተል እነርሱን በማገልገል ዛሬ ከምሰጥህ ትእዛዞች ቀኝም ግራም አትበል።


እርሱና ዘሮቹ በእስራኤል ላይ ረጅም ዘመን እንዲገዙ፥ ከሕጉ ቀኝም ግራም አይበል፤ ራሱን ከሌሎች ወንድሞቹ በላይ የተሻለ አድርጎ አይኩራ።”


በሚያስተምሩህ ሕግና በሚሰጡህ መመሪያዎች መሠረት ፈጽም። ከሚነግሩህ ቀኝም ግራም አትበል።


“ጌታ አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ ለማድረግ ጠንቃቃ ሁኑ፤ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ።


በነገሠም በስምንተኛው ዓመት ገና ብላቴና ሳለ የአባቱን የዳዊትን አምላክ ይፈልግ ጀመር፤ በዓሥራ ሁለተኛውም ዓመት ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ከኮረብታው መስገጃዎችና ከማምለኪያ ዐፀዶቹ፥ ከተቀረፁትና ቀልጠው ከተሰሩት ምስሎች ያነጻ ጀመር።


ነገር ግን የአባቱን አምላክ ፈለገ፥ በትእዛዙም ሄደ፥ እንደ እስራኤልም ያለ ሥራ አልሠራም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios