1 ነገሥት 13:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ኃጢአቱ ለሥረወ መንግሥቱ መጥፋትና በሙሉ ለመደምሰሱ ምክንያት ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ኀጢአት የኢዮርብዓም ቤት እንዲወድቅና ከምድር ገጽም እንዲደመሰስ ምክንያት ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ኃጢአቱ ለሥረወ መንግሥቱ መጥፋትና በሙሉ ለመደምሰሱ ምክንያት ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም ነገር ከገጸ ምድር ለመፍረስና ለመጥፋት በኢዮርብዓም ቤት ላይ ኀጢአት ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስኪፈርስም፥ ከምድርም እስኪጠፋ ድረስ ይህ ነገር ለኢዮርብዓም ቤት ኀጢአት ሆነ። |
በዚህ ምክንያት እነሆ፥ በኢዮርብዓም ቤት ላይ ክፉ ነገርን አመጣለሁ፤ ከቤቱም ነጻም ሆነ ባርያ፥ ወንድ ልጅንም ሁሉ ከእስራኤል አጠፋለሁ፤ ፋንድያን አቃጥለው እንደሚጨርሱት የኢዮርብዓምን ቤት አወድማለሁ።
በከተማይቱ የሚሞተውን ማንኛውንም የቤተሰብህን አባል ውሾች ይበሉታል፤ ገላጣ በሆነው ገጠር የሚሞቱትንም አሞራ ይበላቸዋል፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ጌታ ነኝ።’”
ወደ ኢዮርብዓም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ ጌታ የሚለውን ንገሪው፤ ቃሉም ይህ ነው፤ ‘ከሕዝብ መካከል መርጬ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግኹህ።
ነገር ግን ኢዩ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራውን የንጉሥ ኢዮርብዓምን የኃጢአት መንገድ ከመከተል አልተገታም፤ ኢዩ ራሱ ቀደም ሲል የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በቤትኤልና በዳን ላቆማቸው የወርቅ ጥጃ ምስሎች መስገዱ አልቀረም።
ኢዩ ግን ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ሕግ በፍጹም ልቡ ታዛዥ ሆኖ አልተገኘም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራቸውን የኢዮርብዓምን ክፉ አርአያነት ተከተለ።
እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከይሁዳ ከለየ በኋላ እስራኤላውያን የናባጥን ልጅ ኢዮርብዓምን መርጠው አነገሡ፤ ኢዮርብዓምም እግዚአብሔርን እንዲተው በማድረግ አሠቃቂ ወደ ሆነ ኃጢአት መራቸው፤
የእስራኤል ኃጢአት የሆኑት የአዌን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ እሾኽና አሜከላ በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላል፤ እነርሱም ተራሮችን፦ “ሸፍኑን!” ኮረብቶችንም፦ “ውደቁብን!” ይሉአቸዋል።