1 ነገሥት 13:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከይሁዳ ለመጣው ለእግዚአብሔር ሰው እንዲህ አለው፤ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ጌታ አምላክህ ያዘዘህን ትእዛዝ ባለመታዘዝ የጌታን ቃል አላከበርክም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከይሁዳ ለመጣውም የእግዚአብሔር ሰው፣ “እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፣ ‘የእግዚአብሔርን ቃል አቃልለሃል፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህንም ትእዛዞች አልጠበቅህም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከይሁዳ ለመጣው የእግዚአብሔር ሰው እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዝ ባለመታዘዝ የእግዚአብሔርን ቃል አላከበርክም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከይሁዳም የመጣውን የእግዚአብሔርን ሰው እንዲህ አለው፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእግዚአብሔር ቃል ላይ አምፀሃልና፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ያዘዘህን ትእዛዝ አልጠበቅህምና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከይሁዳም ወደ መጣው ወደ እግዚአብሔር ሰው “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘በእግዚአብሔር አፍ ላይ ዐምፀሃልና፥ አምላክህም እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዝ አልጠበቅህምና፥ |
ስለዚህም ጋድ ወደ ዳዊት ሄዶ፥ “በምድርህ ሦስት ዓመት ራብ ከሚሆን፥ ለሦስት ወር ጠላቶችህ ከሚያሳድዱህና በምድርህ ላይ ለሦስት ቀን የቸነፈር መቅሠፍት ከሚሆን የትኛውን ትመርጣለህ? እንግዲህ አሁን ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አስበህበት ወስን” አለው።
ዖዛ በድፍረት ይህን ስላደረገ፥ የጌታ ቁጣ በላዩ ላይ ነደደ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ቀሠፈው፤ እርሱም በእግዚአብሔር ታቦት አጠገብ እዚያው ሞተ።
ይህን በማድረግ ፈንታ እኔ በዚያ ምንም ዓይነት እህል ውሃ እንዳትቀምስ ወዳዘዝኩህ ቦታ ተመልሰህ በላህ፤ ይህንንም በማድረግህ ምክንያት ትገደላለህ፤ ሬሳህም በቤተሰብህ መቃብር አይቀበርም።’”
ስለዚህም ያ ነቢይ “የጌታን ትእዛዝ መፈጸም እምቢ ስላልክ፥ ከእኔ ተለይተህ እንደ ሄድክ ወዲያውኑ አንድ አንበሳ ይገድልሃል” አለው፤ በእርግጥም ከእርሱ ተለይቶ እንደ ሄደ አንበሳ በድንገት ወደ እርሱ መጥቶ ገደለው።
ክፋትሽ ይቀጣሻል ክህደትሽ ይገሥጽሻል፤ ጌታን አምላክሽን መተውሽ ምን ያኽል ክፉና መራራ ነገር እንደሆነ እወቂም፥ ተመልከቺም፤ እኔን መፍራት በአንቺ ውስጥ የለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ሙሴም አሮንን፦ “ጌታ፦ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ እቀደሳለሁ፥ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ’ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ዝም አለ።
ጌታም ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “በእስራኤል ልጆች ፊት ቅድስናዬን ለማሳየት በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም።”
ሰውየው ስለ እግዚአብሔር ታቦት በተናገረ ጊዜ፥ ዔሊ በቅጥሩ በር አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ በጀርባው ወደቀ፤ እርሱም ያረጀና ሰውነቱም የሚከብድ ስለ ነበር፥ ዐንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እርሱ ለአርባ ዓመት በእስራኤል ላይ ፈራጅ ነበር።