La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 13:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ከአንተ ጋር አብሬ መመለስ አልችልም፤ በዚህም ከአንተ ጋር ምንም ዓይነት እህልም ውሃም አልቀምስም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእግዚአብሔርም ሰው እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ተመልሼ ከአንተ ጋራ አልሄድም፤ በዚህ ቦታም ዐብሬህ እንጀራ አልበላም፤ ውሃም አልጠጣም፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ከአንተ ጋር አብሬ ወደ ቤት መሄድም ሆነ ግብዣህን መቀበል አልችልም፤ በዚህም ከአንተ ጋር ምንም ዐይነት እህል ውሃ አልቀምስም፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም፥ “ከአ​ንተ ጋር እመ​ለ​ስና እገባ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም፤ በዚ​ህም ስፍራ ከአ​ንተ ጋር እን​ጀራ አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም “ከአንተ ጋር እመለስና እገባ ዘንድ አይቻለኝም፤ በዚህም ስፍራ ከአንተ ጋር እንጀራ አልበላም፤ ውሃም አልጠጣም፤

Ver Capítulo



1 ነገሥት 13:16
8 Referencias Cruzadas  

ሽማግሌውም “ወደ ቤቴ መጥተህ ከእኔ ጋር እህል ብላ” አለው።


በለዓምም ሲነጋ ተነሥቶ የባላቅን ሹማምንት፦ “ከእናንተ ጋር እንድሄድ ጌታ አልፈቀደምና ወደ ምድራችሁ ሂዱ” አላቸው።


አሁንም ጌታ ይበልጥ የሚነግረኝን ነገር እንዳውቅ፥ እባካችሁ፥ ሌሎቹ እንዳደረጉት እንዲሁ ዛሬ ሌሊት ደግሞ በዚህ እደሩ።”


እርሱ ግን ዞሮ ጴጥሮስን “ወደ ኋላዬ ሂድ፤ አንተ ሰይጣን! ለእኔ ዕንቅፋት ነህ፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና።” አለው።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ “ሂድ አንተ ሰይጣን ‘ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፎአልና” አለው።


ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት፤ ሰላምም አትበሉት፤