1 ነገሥት 11:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ጌታ የኤዶም ንጉሣዊ ቤተሰብ ወገን የሆነውን ሀዳድን በሰሎሞን ላይ ጠላት አድርጎ አስነሣበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከኤዶም ንጉሣዊ ቤተ ሰብ ኤዶማዊውን ሃዳድን በሰሎሞን ላይ አስነሣው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እግዚአብሔር የኤዶም ንጉሣዊ ቤተሰብ ወገን የሆነውን ሀዳድን በሰሎሞን ላይ ጠላት አድርጎ አስነሣበት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ኤዶማዊው አዴርን ከረምማቴር ወገን የኤልያዳሔ ልጅ ኤስሮምን የሲባ ንጉሥ ጌታውን አድረዓዛርን ጠላት አድርጎ በሰሎሞን ላይ አስነሣ። ሰዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ። የዓመፁም አበጋዝ እርሱ ነበር። ደማስቆንም እጅ አደረጋት። በሰሎሞንም ዘመን ሁሉ በእስራኤል ላይ ጠላት ሆነ። ኤዶማዊው አዴርም ከኤዶምያስ ነገሥታት ዘር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ከኤዶምያስ ነገሥታት ዘር የኤዶምያስን ሰው ሃዳድን ጠላት አድርጎ በሰሎሞን ላይ አስነሣው። |
አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል። በደል በሚፈጽምበትም ጊዜ ሰዎች በሚቀጡበት በትር እቀጣዋለሁ፤ የሰው ልጆችም በዐለንጋ እንደሚገረፉ እገርፈዋለሁ።
ከልጅህም ቢሆን መንግሥቱን በሙሉ አልወስድበትም፤ ለአገልጋዬ ለዳዊትና ለራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል አንድ ነገድ እተውለታለሁ።”
እንደገናም ጌታ ረዞን ተብሎ የሚጠራውን የኤሊዓዳን ልጅ በሰሎሞን ላይ ጠላት አድርጎ አስነሣ፤ ረዞን የጾባ ንጉሥ ከነበረው ከጌታው ከሀዳድዔዜር ኮብልሎ፥
ይህም የሆነበት ምክንያት ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ጌታ የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ንጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን ሐሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት ጌታ ይህን ለውጥ ለማድረግ ስለ ወሰነ ነው።
የእስራኤልም አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፎሐን መንፈስ፥ የአሦርንም ንጉሥ የቴልጌል-ቴልፌልሶርን መንፈስ አስነሣ፤ የሮቤልንና የጋድን ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ አፈለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳሉበት ወደ አላሔና ወደ አቦር፥ ወደ ሃራና ወደ ጎዛን ወንዝ አመጣቸው።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድያምን በሔሬብ ዐለት አካባቢ እንደ መታ፤ በጅራፍ ይገርፋቸዋል፤ በግብጽ እንዳደረገውም ሁሉ፤ በትሩን በውሆች ላይ ያነሣል።
አሁንም ንጉሥ ጌታዬ የባርያውን ቃል ያድምጥ፤ ጌታ በእኔ ላይ አነሣሥቶህ እንደሆነ፥ መሥዋዕት ይቀበል፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ፥ በጌታ ፊት የተረገሙ ይሁኑ፥ ‘ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ’ ብለው በጌታ ርስት ድርሻ እንዳይኖረኝ ዛሬ አሳደውኛልና።