1 ነገሥት 10:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞን ከዚሁ ሰንደል እንጨት የቤተ መቅደሱንና የቤተ መንግሥቱን መከታዎች፥ መዘምራን የሚያገለግሉባቸውን በገናዎችና መሰንቆዎች አሠራ፤ ይህም የሰንደል እንጨት ወደ እስራኤል አገር ከመጣው የሰንደል እንጨት ሁሉ የሚበልጥ ነበር፤ ከዚያም በኋላ ይህን የመሰለ የሰንደል እንጨት ከቶ ታይቶ አያውቅም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም የሰንደሉን ዕንጨት ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና ለቤተ መንግሥቱ መደገፊያ፣ ለመዘምራኑ የመሰንቆና የበገና መሥሪያ አደረገው። ይህን ያህል ብዛት ያለው የሰንደል ዕንጨት እስከ ዛሬ ድረስ ከቶ አልመጣም፤ አልታየምም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞን ከዚሁ ሰንደል እንጨት የቤተ መቅደሱንና የቤተ መንግሥቱን መከታዎች፥ መዘምራን የሚያገለግሉባቸውን በገናዎችና መሰንቆዎች አሠራ፤ ይህም የሰንደል እንጨት ወደ እስራኤል አገር ከመጣው የሰንደል እንጨት ሁሉ የሚበልጥ ነበር፤ ከዚያም በኋላ ይህን የመሰለ የሰንደል እንጨት ከቶ ታይቶ አያውቅም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ከተጠረበው እንጨት ለእግዚአብሔር ቤትና ለንጉሡ ቤት መከታ፥ ለመዘምራኑም መሰንቆና በገና አደረገ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በምድር ላይ እንደዚያ ያለ የተጠረበ እንጨት ከቶ አልመጣም፤ በየትም ቦታ አልታየም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለእግዚአብሔር ቤትና ለንጉሡ ቤት መከታ፥ ለመዘምራኑም መሰንቆና በገና አደረገ፤ እስከ ዛሬም ድረስ እንደዚያ ያለ የሰንደል እንጨት ከቶ አልመጣም፤ አልታየምም። |
ንጉሥ ሰሎሞን ከተለመደው የልግስና ስጦታው ጋር የሳባ ንግሥት የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣት፤ ከዚህ በኋላ ንግሥተ ሳባ ከክብር አጃቢዎችዋ ጋር ወደ አገርዋ ተመልሳ ሄደች።
ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለጌታ ቤትና ለንጉሡ ቤት እርከኖችን፥ ለመዘምራኑም መሰንቆና በገና ሠራ፤ እንደዚህም ያለ በይሁዳ ምድር ከቶ አልታየም ነበር።