1 ነገሥት 1:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጃገረዲቱም እጅግ ውብ ነበረች። ለንጉሡም ረዳትና አገልጋይ ሆነች፤ ንጉሡ ግን ከእርሷ ጋር ግንኙነት ፈጽሞ አያውቅም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጃገረዲቱ እጅግ ቈንጆ ነበረች፤ ንጉሡንም ትንከባከበውና ታገለግለው ነበር፤ ንጉሡ ግን ከርሷ ጋራ ግንኙነት አልነበረውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም እጅግ ውብ ነበረች፤ ከንጉሡም ጋር ሆና በማገልገል ትንከባከበው ነበር፤ ይሁን እንጂ እርሱ ከእርስዋ ጋር አልተገናኘም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቆንጆዪቱም እጅግ ውብ ነበረች፤ ንጉሡንም ታቅፈውና ታገለግለው ነበር፤ ንጉሡ ግን አያውቃትም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቆንጆይቱም እጅግ ውብ ነበረች፤ ንጉሡንም ትረዳውና ታገለግለው ነበር፤ ንጉሡ ግን አያውቃትም ነበር። |
ያንጊዜ የሐጊት ልጅ አዶንያስ፦ “ንጉሥ እሆናለሁ” ብሎ ተነሣሣ፤ ለራሱም ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን፥ እንዲሁም ኀምሳ ጋሻ ጃግሬዎችን አዘጋጀ።
እርሱም “ንጉሥ ሰሎሞን አንቺን እምቢ እንደማይልሽ ዐውቃለሁ፤ ስለዚህ አቢሻግ ተብላ የምትጠራውን ሹኔማይት ልጃገረድ በሚስትነት እንዲድርልኝ እባክሽ አማልጅኝ” አላት።