1 ነገሥት 1:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ብዙ በሬዎችንና ፍሪዳዎችን በጎችንም ሠውቶአል፥ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ ካህኑንም አብያታርን፥ የሠራዊቱንም አለቃ ኢዮአብን ጠርቶአል፥ ባርያህን ስሎሞንን ግን አልጠራውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ በሬዎችን፣ ኰርማዎችንና በጎችን በብዛት ሠውቷል፤ የንጉሡን ልጆች በሙሉ፣ ካህኑን አብያታርንና የሰራዊቱን አዛዥ ኢዮአብን ጠርቷል፤ አገልጋይህን ሰሎሞንን ግን አልጠራውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ብዙ ኰርማዎችን፥ የሰቡ ወይፈኖችንና በጎችን መሥዋዕት አቅርቦአል፤ በበዓሉም ላይ እንዲገኙለት የንጉሡን ልጆች ካህኑን አብያታርንና የሠራዊትህን አዛዥ ኢዮአብን ጋብዞአቸዋል፤ አገልጋይህን ሰሎሞንን ግን አልጋበዘውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ብዙ በሬዎችንና ጠቦቶችን፥ በጎችንም ሠውቶአል፤ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ ካህኑንም አብያታርን፥ የሠራዊቱንም አለቃ ኢዮአብን ጠርቶአል፤ ባሪያህን ሰሎሞንን ግን አልጠራውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ብዙ በሬዎችንና ፍሪዳዎችን በጎችንም ሠውቶአል፤ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ ካሁኑንም አብያታርን፥ የሠራዊቱንም አለቃ ኢዮአብን ጠርቶአል፤ ባሪያህን ስሎሞንን ግን አልጠራውም። |
እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬዎችንና ፍሪዳዎችን በጎችንም ሠውቶአል፥ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ የሠራዊቱንም አለቃ ኢዮአብን። ካህኑንም አብያታርን ጠርቶአል፥ እነሆም፥ በፊቱ እየበሉና እየጠጡ፦ ‘አዶንያስ ሺህ ዓመት ይንገሥ’ ይላሉ።
ሌሎች ባርያዎችን ደግሞ ልኮ ‘የታደሙትን እነሆ ድግሴን አዘጋጅቻለሁ፤ ሰንጋዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ግብዣ ኑ፤ በሉአቸው፤’ አለ።