ከዚያም ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ወደ እርሷም ገብቶ አብሮአት ተኛ፤ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሰሎሞን አለው። ጌታም ወደደው፤
1 ነገሥት 1:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ነቢዩን ናታንን፥ በናያስንም፥ ኃያላኑንም፥ ወንድሙንም ሰሎሞንን አልጠራም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ነቢዩ ናታንንም ሆነ በናያስን፣ የክብር ዘበኞቹንም ሆነ ወንድሙን ሰሎሞንን አልጠራም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ነቢዩን ናታንን፥ በናያን፥ የንጉሡን የክብር ዘበኞችና ወንድሙን ሰሎሞንን አልጠራቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ነቢዩን ናታንን፥ በናያስንም፥ ኀያላኑንም፥ ወንድሙንም ሰሎሞንን አልጠራም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ነቢዩን ናታንን፥ በናያስንም፥ ኀያላኑንም፥ ወንድሙንም ሰሎሞንን አልጠራም። |
ከዚያም ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ወደ እርሷም ገብቶ አብሮአት ተኛ፤ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሰሎሞን አለው። ጌታም ወደደው፤
እርሱም ብዙ በሬዎችንና ፍሪዳዎችን በጎችንም ሠውቶአል፥ የንጉሡንም ልጆች ሁሉ፥ ካህኑንም አብያታርን፥ የሠራዊቱንም አለቃ ኢዮአብን ጠርቶአል፥ ባርያህን ስሎሞንን ግን አልጠራውም።
የሐጊት ልጅ አዶንያስ ወደ ሰሎሞን እናት ወደ ቤርሳቤህ ሄደ፤ ቤርሳቤህም “ወደ እኔ የመጣኸው በሰላም ነውን?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም “አዎን በሰላም ነው የመጣሁት” ሲል መለሰ።