1 ቆሮንቶስ 7:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚስት ሆይ! ባልሽን ታድኚ እንደሆን ምን ታውቂያለሽ? ወይስ ባል ሆይ! ሚስትህን ታድን እንደሆንህ ምን ታውቃለህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንቺ ሴት፤ ባልሽን ታድኚው እንደ ሆነ ምን ታውቂያለሽ? ወይስ አንተ ሰው፤ ሚስትህን ታድናት እንደ ሆነ ምን ታውቃለህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንቺ ክርስቲያን ሴት፥ ክርስቲያን ያልሆነውን ባልሽን ምናልባት ታድኚው እንደ ሆነ ምን ታውቂያለሽ? አንተስ ክርስቲያን ወንድ፥ ክርስቲያን ያልሆነች ሚስትህን ምንአልባት ታድናት እንደ ሆንክ ምን ታውቃለህ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሚስትም ባልዋን ታድነው እንደ ሆነ አታውቅምና፤ ባልም ሚስቱን ያድናት እንደ ሆነ አያውቅምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንቺ ሴት፥ ባልሽን ታድኚ እንደ ሆንሽ ምን ታውቂአለሽ? ወይስ አንተ ሰው፥ ሚስትህን ታድን እንደ ሆንህ ምን ታውቃለህ? |
ደካሞችን መጥቀም እንድችል ለደካሞች እንደ ደካማ ሆንኩ፤ በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን ማዳን እንድችል፥ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ።