እኔ የምለው፥ እያንዳንዳችሁ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፤” “እኔስ የአጵሎስ ነኝ፤” “እኔ ግን የኬፋ ነኝ፤” “እኔስ የክርስቶስ ነኝ፤” ትላላችሁ።
1 ቆሮንቶስ 3:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዱ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፤” ሌላው ደግሞ “እኔ የአጵሎስ ነኝ፤” ቢል ሰዎች ብቻ መሆናችሁ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም አንዱ፣ “እኔ የጳውሎስ ነኝ”፣ ሌላው ደግሞ፣ “እኔ የአጵሎስ ነኝ” ቢል፣ ሥጋ ለባሽ ብቻ መሆናችሁ አይደለምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዱ “እኔ የጳውሎስ ነኝ” ሌላው ደግሞ “እኔ የአጵሎስ ነኝ” ሲል ተራ የዓለም ሰዎች ብቻ መሆናችሁ አይደለምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመካከላችሁ፥ “እኔ የጳውሎስ ነኝ” የሚል አለና፤ ሌላውም፥ “እኔ የአጵሎስ ነኝ” ቢል እናንተ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱ፦ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ ሁለተኛውም፦ እኔ የአጵሎስ ነኝ ቢል ሰዎች ብቻ መሆናችሁ አይደለምን? |
እኔ የምለው፥ እያንዳንዳችሁ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፤” “እኔስ የአጵሎስ ነኝ፤” “እኔ ግን የኬፋ ነኝ፤” “እኔስ የክርስቶስ ነኝ፤” ትላላችሁ።
ወንድሞች ሆይ! ስለ አንዱ በሌላው ላይ አንዳችሁም እንዳትታበዩ “ከተጻፈው አትለፍ፤” የሚለውን በእኛ እንድትማሩ፥ በዚህ ስለ እናንተ ስል ራሴንና አጵሎስን እንደ ምሳሌ ተናገርሁ።