1 ቆሮንቶስ 3:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም፥ ሁሉ ነገር የእናንተ ነውና፥ ማንም በሰው አይመካ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ማንም በሰው አይመካ። ሁሉ ነገር የእናንተ ነውና፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሁሉ ነገር የእናንተ ስለ ሆነ ማንም በሰው አይመካ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም እንግዲህ አንዱ ስንኳ በሰው አይመካ፤ ሁሉ የእናንተ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም ማንም በሰው አይመካ። ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤ |
ወንድሞች ሆይ! ስለ አንዱ በሌላው ላይ አንዳችሁም እንዳትታበዩ “ከተጻፈው አትለፍ፤” የሚለውን በእኛ እንድትማሩ፥ በዚህ ስለ እናንተ ስል ራሴንና አጵሎስን እንደ ምሳሌ ተናገርሁ።